ኢሳያስ የኤርትራ ህዝብ ክብርና ሉኣላዊነት የደፈረ እና ያዋረደ ነው ሲል ኤርትራዊው ልኡል ጋይም ገለፀ ፡፡
——
አምባገነኑ ኢሳያስ የሚመራው የህግደፍ ስርኣት የኤርትራ ህዝብ ክብርና ሉኣላዊነት የደፈረ እና ያዋረደ ነው ሲል ለዓመታት የአምባገነኑን ስርኣት በመቃወም ላይ የሚገኘው ኤርትራዊው ልኡል ጋይም ገለፀ ፡፡
የኤርትራ ህዝብ ተታሎ በማይመለከተው ጦርነት በመግባቱ እጁን ሊሰጥ ካልሆነ ወሮ ከያዘው መሬት በመውጣት የዚህ ወንጀለኛ ስርኣት ተባባሪ ከመሆን ሊቆጠብ ይገባል ብለዋል፡፡
ኣምባገነኑ ኢሳያስ የኤርትራ ህዝብ ለዓመታት ከየትኛውም አለም ተገልሎ እንዲኖር ከማድረግ ባሻገር የሃገሪቱ ኢኮኖሚ በማድቀቅ ህዝቡን ለማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ዳርጓታል፤ ከዚህ በተጨማሪም ህፃናትንና ወጣቶች የማደናገርያ ፕሮፖጋንዳ በመንዛት ወደ ማይመለከታቸው ጦርነት በማስገባት በሃገሪቱ አምራች ትውልድ እንዳይኖር አድርጓል ይላሉ ለረጅም ጊዚያት ስርኣቱን በመቃወም የሚታወቁ አቶ ልኡል ጋይም ፡፡
አቶ ልኡል ጋይም ከዝግጅት ክፍላችን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደ አምባገነኑ ኢሳያስ የሚመራው የህግደፍ ስርኣት የኤርትራ ህዝብ ክብርና ሉኣላዊነት የደፈረም ሆነ ያዋረደ ስርኣት የለም በማለት ይገልፃል ፡፡
ኤርትራዊው ታጋይ አያይዘውም የህግደፍ ስርኣት ሰላልቻለ ነው እንጂ ቢችል ኖሮ የትግራይ ህዝብን ኦክስጅንም በመከልከል በሶስት ደቂቃ ውስጥ እንደ ህዝብ እንዲጠፋ እና በመሬቱም ሰው እንዳይኖር የማድረግ ፍላጎት እንደነበረው ገልፀዋል፡፡
የኤርትራ ህዝብ ተታሎ በማይመለከተው ጦርነት መግባቱን የሚገልፁት አቶ ሉኡል ኤርትራዊ ወጣት እጁን እንዲሰጥ ካልሆነ ወሮ ከያዘው የትግራይ መሬት ለቆ በመውጣት የዚህ ወንጀለኛ ስርኣት ተባባሪ ከመሆን ሊቆጠብ እንዲሚገባ ኤርትራዊው ታጋይ ሉኡል ጋይም አሳስበዋል፡፡
ፍሬሂወት ተ/መድህን