Home ዜና የዘንድሮው የአል-ነጃሺ በዓል በከበባና ክልከላ ምክንያት እንደወትረው ማክበር እንዳልተቻለ ተገለፀ።

የዘንድሮው የአል-ነጃሺ በዓል በከበባና ክልከላ ምክንያት እንደወትረው ማክበር እንዳልተቻለ ተገለፀ።

1593
0

የፋሽስት ቡድኑ በትግራይ ባኖረው ከበባና ክልከላ ምክንያት በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው በትግራይ የአል ነጃሽን ዓሹራ በዓል የዘንድሮው የ1445 ዓመተ ሂጅራ  አከባበር ከወትሮው መቀዛቀዙን ተገለፀ፡፡

አል-ነጃሺ በመላው ዓለም በሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ክብር ያለው  ሃይማኖታዊ እና ታሪካዊ  ቅርስ እንደመሆኑ መጠን በየአመቱ በሚከበረው  የዓሹራ በዓል ከሩቅም ከቅርብም ከበርካታ ሀገራት ለጉብኝት(ለዚያራ) ፀሎታቸውን(ዱዓ) ለማድረስ  በመምጣት  በበጎ የመተጋገዝና የመረዳዳት ስርዓታቸው የሚከውኑበት እንደነበረ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ በትግራይ ህዝብ ላይ ከታወጀው የጀኖሳይድ ጦርነት እንዲሁም ዝርፍያና ከፍተኛ የቅርስ ውድመት ከደረሰበት አንዱ ሃይማኖታዊ እና ታሪካዊ መስጂድና መካነ መቃብር መሆኑም በማስታወስ ዘንድሮ ግን ከወትረው ባነሰ መልኩ ለማክበር ተመክረዎል።፡

በመጨረሻም ይህን ፈተና አልፎ ከዚሁ ካጋጠመው ችግር ሳይምበረከኩ  ከችግሩ በመማር በወኔና በፅናት እንደሚታገሉ፤ እንደ እምነታቸው መሰረት ድል የተበደሉ መሆኑን በማስታወስ በመላው ዓለም የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች የዘንድሮው ለ1445 ዓመተ ሂጅራን  እንኳን ለአል-ነጃሽ የዓሹራ በዓል አደረሳቹ በማለት ታላቅ ምኞታቸው አሰምተዋል፡፡      በሃይለኪሮስ ወልዳይ

Previous articleالإتحاد الأفريقي يستضيف الأمم المتحدة الأوروبي لإحلال السلام بين حكومة تقراي و الحكومة الفيدرالية الأثيوبية
Next articleወፍሪ ልምዓት ድንሽን ሽኮር ድንሽን  “Potato Revolution” ወያነ ድንሽ