Home ዜና የትግራይ ህዝብ የገጠመውን ፈተና እንደየ አመጣጡ እየመከተ አይበገሬነቱ አስመስክረዋል ሲሉ አቶ ጌታቸው...

የትግራይ ህዝብ የገጠመውን ፈተና እንደየ አመጣጡ እየመከተ አይበገሬነቱ አስመስክረዋል ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ገለፁ፡፡

786
0

የትግራይ ህዝብ የገጠመውን ፈተና እንደየ አመጣጡ እየመከተ አይበገሬነቱ አስመስክረዋል ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ገለፁ፡፡

——

አምና በዚህ ሳምንት የተጀመረው እና መቐለን ጨምሮ አብዛኛውን ትግራይ ነፃ ያደረገው በአፍሪካዊው ጄኔራል ራስ አሉላ አባ ነጋ የተሰየመው ዘመቻ የትግራይ ህዝብን ጠላቶች የማይረሱት ትምህርት የሰጠ እና የትግራይ ህዝብም ነፃነቱን ለማንም አሳልፎ የማይሰጥ መሆኑን ያስመሰከረበት እና ታሪካዊ አይበገሬነቱን ያሳየበት ታሪካዊ ዘመቻ እንደነበር የትግራይ ሴንትራል ኮማንድ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ገለፁ።

አቶ ጌታቸው በወቅታዊ ጉዳይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ  የትግራይ ህዝብ የገጠመውን ፈተና እንደየ አመጣጡ እየመከተ፤ ሊያንበረክኩት የሚመጡ ጠላቶችም ደጋግመው እንዲያስቡ እና የማይረሱት ትምህርት የወሰዱበት መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ጌታቸው አክለውም የትግራይ ህዝብ የፀረ ጭቆና እና ፀረ ባርነት የነፃነት ተጋድሎ በትውልድ ቅብብሎሽ እየቀጠለ መሆኑ በተግባር የተረጋገጠበት ወቅት ነው ብለዋል።

ዘመቻ አሉላ የትግራይ ሰራዊት እንደ ዱቄት ጠፍቷል ተበትኗል ሲባል የነበረው ጠላት ሲመካበት የነበረውን ሁሉንም አቅሙ በቀናት ውስጥ አፈራርሶ የትግራይ ህዝብ ክብርን ከፍ በማድረግ መቐለን ጨምሮ አብዛኛው ትግራይን ነፃ ያወጣ ዘመቻ ነበር ያሉት አቶ ጌታቸው የትግራይ ህዝብ ህጋዊ መንግስቱ ወደ መንበሩ እንዲመለስ ያስቻለ ዘመቻ ነበር ብለዋል።

አሁንም ቢሆን የትግራይ ህዝብን ወደ ለየለት ግጭት ለማስገባት እና የሰላም ጭላንጭል ለማጥፋት የሚተነኩሱ ሃይሎች አልጠፉም ያሉት አቶ ጌታቸው ለነዚህ ትንኮሳዎች ምላሽ ከመስጠት ባለፈ ተጣድፈን ወደ ግጭት ላለመግባት እየጣርን ነው ብለዋል።

የትግራይ ህዝብ ወትሮም ለሰላም የፀና እና ቁርጠኛ አቋም አለው የትግራይ ህዝብ መሰረታዊ ፍላጎቶቹ እና ጥቅሞቹ በሰላም የሚፈቱ ከሆነ አማራጩን እንጠቀማለን ካልሆነ ግን የትግራይ ህዝብ ህልውና በሰላም አልያም በሌላ መንገድ ይረጋገጣል ሲሉ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

በየአመቱ ሰኔ 15 የሚከበረው እና ዘንድሮ ለ34ኛ ግዜ የሚከበረው የትግራይ ሰማእታት ቀን አዲስ ሰማእታት ያስተናገድንበት ሆኗል ያሉት አቶ ጌታቸው የትላንትም የዛሬም ሰማእታት አደራ በመቀበል የትግራይ ህዝብ ህልውና እና ጥቅም ወደ ኃላ የማይቀለበስበት ደረጃ ለማድረስ የትግራይ ህዝብ ሰራዊቱ እና መንግስቱ ሁሌም ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።

Previous articleበፋሽስቱ የአብይ ቡዱን የጄኖሳይድ ጦርነት ማብቂያ ሳይበጅለት የአለም ባንክ ለመስጠት ያቀደው የገንዘብ ድጋፍ ሊታሰብበት እንደሚገባ  ተጠየቀ፡፡
Next articleኢሳያስ የኤርትራ  ህዝብ ክብርና ሉኣላዊነት የደፈረ እና ያዋረደ ነው ሲል ኤርትራዊው ልኡል ጋይም ገለፀ ፡፡