Home ዜና የኢሮብ ብሄረሰብ ሰቆቃ

የኢሮብ ብሄረሰብ ሰቆቃ

1465
0

በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የኢሮፕ ወረዳ 33 ሺህ ነዋሪዎች በምግብ እጥረት ምክንያት ለከፍተኛ ረሃብ መጋለጣቸው ተገለጸ፡፡

በመጋቢት ወር ብቻ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን በግጭትና በምግብ እጦት ሳብያ ከ87 ሺህ በላይ ህዝብ ቤት ንብረቱን ጥሎ ለመሰደድ ተገዷል ሲል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት OCHA ማስታወቁን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡

በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ኢሮፕ ወረዳ በምግብ እጦት ሳብያ 65 በመቶ የወረዳው ህዝብ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጧል ሲል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት OCHA ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ኦቻን ጠቅሶ Addis standared እንደዘገበው በትግራይ ህዝብ ላይ በተጣለው ከበባና ክልከላ ምክንያት በትግራይ ከሚኖሩ ብሔሮች አንዱ የሆነው የኢሮፕ ብሄረሰብም የዚህ ችግር ገፈት ቀማሽ ሆኗል ብሏል፡፡

የኢሮፕ ወረዳ  ለኤርትራ አዋሳኝ አካባቢ መሆኑ ተከትሎ የአምባገነኑ ኢሳያስ አፈወርቂ ወታደሮች ወረዳውን በመውረር የህዝቡን ንብረት ሙሉ በሙሉ በመዝረፋቸው እና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን በማውደማቸው ህዝቡ ለከፍተኛ ችግር ተዳርጓል፤ የሚደረግው ሰብአዊ ድጋፍም አነስተኛ ነው ብሏል OCHA ፡፡

በዚህም በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የኢሮፕ ወረዳ 33 ሺህ ህዝብ በምግብ እጦት ሳብያ  ለከፍተኛ ችግር ተጋልጧል ነው ያለው ፡፡

በትግራይ ካሉት ፓርቲዎች አንዱ የሆነው የአሲምባ ዲሞክራቲክ ፓርቲ የኢሮፕ ማህበረሰብ ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ትግራይን ከወረረ ጀምሮ በአምባገነኑ ኢሳያስ አፈወርቂ ወታደሮች ከፍተኛ ግፍና በደል ተፈጽሞበታል አሁንም እየተፈጸመበት እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

የአሲምባ ዲሞክራቲክ ፓርቲ መሪ በኢሮፕ ወረዳ የአምባገነኑ የኢሳያስ ወታደሮች ወረራ እየፈጸሙ ነው በማለታቸው ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ይፋዊ ጦርነት ከጀመረ ጀምሮ እስከአሁን በአዲስአበባ በእስር እንደሚገኙ ፓርቲው አስታውቋል፡፡

እውነት በመናገራቸው ምክንያት በእስር ላይ የሚገኙት የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ ዶሪ አስገዶም በአስቸኳይ እንዲፈቱ የአሲምባ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ባለፈው ሳምንት ጥሪ ማቅረቡንም Addis standaredበዘገባው አስታውሷል፡፡

ይህ በአንዲህ እንዳለ አምባገነኑ ኢሳያስ አፈወርቂ እያደረገው ባለው ትንኮሳ ምክንያት   ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ከ87 ሺህ በላይ የትግራይ ተወላጆች ቤት ንብረታቸውን ጥለው  ለመሰደድ ተገደዋል ብሏል፡፡

በምስራቅ፣ በሰሜን ምዕራብ እና በምዕራብ ትግራይ እና የኤርትራ አዋሳኝ አከባቢዎች ወታደራዊ ትንኮሳዎች እየተፈጸሙ በመሆናቸው ለህዝቡ አርዳታ ለማድረስ አዳጋች መሆኑንም ዘገባው አመላክቷል፡፡

በምዕራብ ትግራይ የሱዳን ድንበር ሀሚዳይት አቅራብያ በበረከት፣ ማይ ካድራና በሁመራ የተኩስ ልውውጦች በመኖራቸው በቦታው የነበሩ የሰብአዊ እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች በጊዜያዊነት ደህንነቱ ወደ ተጠበቀ ቦታ ለመዘዋወር መገደዳቸውም OCHA ይፋ አድርጓል፡፡

ጦርነቱ በእነማን መካከል እየተደረገ ስለመሆኑ ግን በዘገባው ላይ አልተካተተም፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በቆራሪት፣ ማይገባ፣ ወልቃይትና አከባቢባው ሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ አስቸጋሪ ሆኗል ብሏል፡፡

በሽሬ አካባቢ እና በሰሜን ምዕራብ ትግራይ በተለኮሰው ግጭት በንጹሃን ዜጎች ጉዳት መድረሱንና የአንድ ሰብአዊ እርዳታ አቅራቢ ድርጅት ህንጻ መውደሙንም OCHA አስታውቋል፡፡

በእነዚህ አካባቢዎች የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለወራት ምንም አይነት እርዳታ ማግኘት አልቻሉም በዚህም ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠዋል ሲል OCHA ጠቅሶ Addis standared አስነብቧል፡፡

Previous articleብዓመፅ ማህፀና ዝወረዳ ትግራወይቲ
Next articleትንሳኤ ትግራይ