Home ዜና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የአፍሪካ ህብረት በኦሮሚያ ያለውን ወታደራዊ ግጭት የብሄር ብጥብጥ ነው...

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የአፍሪካ ህብረት በኦሮሚያ ያለውን ወታደራዊ ግጭት የብሄር ብጥብጥ ነው ብሎ መፈረጁን ወቀሱ።

960
0

—-

የአፍሪካ ህብረት በቅርቡ ባወጣው አጭር ማስታወሻ የህብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ኦሊሴጐን ኦባሳንጆ ለህብረቱ የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት ያቀረቡትን ማብራሪያን ተከትሎ ህብረቱ በኦሮሚያ ያለውን ወታደራዊ ግጭት የብሄር ግጭት ብሎ መግለፁ ከአንድ ትልቅ የአህጉሪቱ ተቋም የማይጠበቅ የተሳሳተ ግምትና የተዛባ አመለካከት ላይ የተመሠረተ እንዲሆነም አመላክቷል።

አንድ ታዛቢ ከአፍሪካ ህብረት የሚጠብቀው ለግጭቱ መንሥኤ የሆኑ መሰረታዊ ምክንያቶችና የግጭቱ ተዋንያን በተመለከተ ከአድልዎ ነፃ ሆነ ጠንካራና አጠቃላይ ትንተና ላይ የተመሠረተ መደምደሚያ ላይ እንዲደርስ ነው ብሏል መግለጫው።

የአፍሪካ ህብረት ድምዳሜ በኦሮሚያ በአጠቃላይ እና በምዕራብ ኦሮሚያ ደግሞ በተለይ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር በሰላም አብረው የኖሩትን የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችና ማንነቶችን ሁኔታ ግምት ውስጥ ያላስገባ እንደሆነም መግለጫው ጠቅሶ ከጥንት ከጠዋቱ የኦሮሞ ህዝብ የእንግዳ አቀባበል እና ወዳጅነት እንዲሁም ከኦሮሞ ብሄር ውጭ ያሉት ቡዱኖች አቅፎ የማኖሩን ባህል ጋር የሚጋጭ መደምደሚያ መሆኑንም አስረድቷል መግለጫው።  

Previous articleበፋሽስቱ የአብይ ቡድን እና በደቡብ ክልል የመንግስት ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት የበርካታ ሂወት መጥፋቱ ተገለፀ።
Next articleበኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፈን አሜሪካ በትኩረት እየሰራች መሆኗን ተገለፀ፡፡