Home ዜና በመቐለ  መዋእለ ህፃናት ከተካሄደው የአየር ድብደባ በህይወት የተረፉት ህፃናት በከፍተኛ የአእምሮ መረበሽ...

በመቐለ  መዋእለ ህፃናት ከተካሄደው የአየር ድብደባ በህይወት የተረፉት ህፃናት በከፍተኛ የአእምሮ መረበሽ ውስጥ እንደሚገኙ ተገለፀ።

1083

ፋሽስቱ አብይ አሕመድ በህፃናት መዝናኛ ስፍራና በኤስ ኦ ኤስ መዋእለ ህፃናት ላይ ባደረሰው የአየር ድብደባ ህፃን አርያም ሀፍቱ ጉዳት ከደረሰባቸው አንዷ ናት፡፡

ህፃንዋ ከደረሰባት የአካል ጉዳት በተጨማሪ በአደጋው ወንድሟን በማጣትዋ በከፍተኛ የአይምሮ መቃወስ ውስጥ እንደምትገኝ ቤተሰቦችዋ ይገልፃሉ፡፡       

ፋሽስቱ የአብይ አሕመድ ቡድን በሰላማውያን ዜጎች ላይ ሆን ብሎ በማነጣጠር በህፃናት መዝናኛ ስፍራና በኤስ ኦ ኤስ መዋእለ ህፃናት እንዲሁም በሰለማውያን መኖርያ ቤቶች ላይ ባደረሰው የአየር ድብደባ አርያም ሀፍቱ ጉዳት ከደረሰባቸው ህፃናት አንዷ ነች፡፡ በአደጋውም እሷ ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ ወንድሟን በሞት አጥታለች፡፡

ህፃንዋን ከሞት ያተረፋት አጎትዋ አቶ ብርሀኑ ሕሸ በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ እንዲህ ገልፀዋል፡፡ 

ህፃን አርያም ሀፍቱ በአደጋው ወቅት ባየችው አሰቃቂ ሁኔታና የወንድሟ ሞትም ተጨምሮባት በከፍተኛ የአይምሮ መቃወስ ውስጥ እንደምትገኝ አቶ ብርሀኑ ይናገራል፡፡

ከፋሽስቱ የአብይ ቡድን የአየር ድብደባ ላይ በተአምር የተረፉት በአካባው ነዋሪ የሆኑት ህፃናት በበኩላቸው የነበረው አደጋ ከባድ እንደነበር ገልፀው አሁን በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ እንዳሉ ይገልፃሉ፡፡

በመሆኑም የአለም ማህበረ-ሰብ የትግራይ ህዝብ እየደረሰበት ያለውን እልቂት እና ፋሽስቱ ቡድን የጦርነት ሕግ በመጣስ እየፈፀመው ያለው ወንጀል ተገንዝቦ በፋሽስቱ አብይ አሕመድ ቡድን ላይ ድርጊቱን ሊያስቆም የሚችል ተጨባጭ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል ብለዋል፡፡

ዊንታ ዘላለም