Home ዜና የማህብራዊ ሚድያ ውሎ፡፡

የማህብራዊ ሚድያ ውሎ፡፡

815

መንግስታዊ ድጋፍ ያለውና ፅንፈኛ የፋኖ ቡድን በጎንደር ከተማ በሙስሊም ማህበረ-ሰብ ላይ የፈፀመው ጭፍጨፋ በዛሬ እለት የማህበራዊ ሚድያ መነጋገሪያ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ ሆኖ ውለዋል፡፡

የትግራይ ህዝብ በወራሪዎች ሲጨፈጭፍ እና ታሪካዊ የነጋሽ መስጊድ ጨምሮ በርካታ ሃይማኖታዊ እና ታሪካዊ ቅርሶች ሲወድሙ  ከኢትዮጵያ አይበልጥብንም በማለት ዝምታ መምረጣቸውን በማስታወስ  አሁን በጎንደር ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ ጭፍጨፋ ሲደርስ ችግሩ ኢትዮጵያዊ ስሪቱ ውስጥ የተደበቀ ጥላቻ ነው በማለት ሃሳባቸውነ የሰነዘሩ በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡

በፅንፈኛው ፋኖ በጎንደር ከተማ በተፈፀመው ጥቃት 21 ሰዎች መሞታቸው እና ከ150 በላይ ሰዎች መቁሰላቸው ተከትሎ በተለያዩ የማህበረ-ሰብ ክፍሎች ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡

በተለይ ደግሞ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘነድ በርካታ አስተያየቶች እየተሰጡ ሲሆነ የአል-ነጃሺ መሲጊድ በወራሪዎች ሲወድም ዝምታን የመረጡ እና አሁን በጎንደሩ ድርጊት እየታየ ያለው ጭሁትን እያነፃፀሩ የተቹም አልጠፉም፡፡

በፋስ ቡክ ገፅ ላይ ቲም ቫንዳን በተባለ ስም የሚታወቁት ፀሃፊ እንዳሉት ድርጊቱ በጎንደር ከተማ  በሰለማውያን የሙስሊም ማህበረ-ሰብ ላይ ብቻ የተፈፀመ ጭፍጨፋ አይደለም ብለውታል፡፡

ጭፍጨፋውና ዘረፋው በትግራይ ምእራባዊ ዞንና  በሰሜናዊ ምእራብ ትግራይ ፀለምቲ ወረዳ እንዲሁም  በጎንደር ዙሪያ በሚገኙ የቅማንትና ሌሎች ህዝቦች ላይ ፅንፈኛው የፋኖ ቡድን  እየጨፈጨፉ መጥተዋል፡፡ አሁንም ቀጥሎበታል ሲል ሃሳቡን አስፍሯል፡፡

መንግስታዊ ደጋፍ ያለው ፋኖ የተባለው ፅንፈኛ የአማራ ተስፋፊ ቡድን በረመዳን ፆም ሙስሊም ማህበረ-ሰብን ጨፍጭፈዋል ያሉት ደግሞ በፌስ ቡክ ገፃቸው አክመል ነጋሽ በሚል ስም የሚታወቁ ፀሀፊ ናቸው፡፡

ፀሃፊው እንዳሉት ፅንፈኛ ቡድኑ በትግራይና በኦሮሚያ ህዝብ ላይ ለመገመት የሚያዳግት ጭፍጭፋ እንደፈፀመ ጠቅሰው ጭካኔው አብረውት በሚኖሩና በጎረቤቱ ህዝቦች ላይ ተመሳሳይ ግፍ እየፈፀመ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ፆመኞችን በጥይት ያስፈጠረች ብቸኛ ከተማ ጎንደር ከተማ መሆኗን የገለፁት ደግሞ በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች   ናቸው፡፡

አማነ ባድሃሶ የተባሉ ፀሀፊ በበኩላቸው በጎንደር ሰላማውያን የሙስሊም ማህበረ-ሰብ ላይ ጭካኔ የተሞላበት ጭፍጨፋ መፈፀሙን ተከትሎ በጣም ደንግጫለሁ ብለዋል፡፡

በርካታ መስጊዶችም በእሳት ጋይተዋል ድርጊቱ የእስልምና  ሃይማኖት ላይ ጥላቻ ያላቸው የአሸባሪነት ስራ የተላበሱ ሰዎች ናቸው ብለዋል፡፡

ተመስገን ገመቹ የተባሉ ፀሀፊ ደግሞ በታሪካዊ የነጋሽ መስጊድ ፋኖ የተባለ ፅንፈኛ ቡድን ሲያወድመውና የትግራይ ህዝብ ሲጨፈጭፍ ከኢትዮጵያ አይበልጥብንም በማለት ዝምታ እንደተመረጠ አስነብበውናል፡፡

አሁን በጎንደር ሙስሊም ማህበረ-ሰብ ላይ ጭፍጨፋ ሲደርስ ችግሩ ኢትዮጵያዊ ስሪቱ ውስጥ የተደበቀ ጥላቻ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ፍቅር  የጥላቸው መሸፈኛ ቅብ መሆኑን በመግለፅ በኢትዮጵያ ስም አገርን ትርምስ ውስጥ የከተትዋት ተስፋፊና አክራሪ የአማራ ሀይሎችን  ተጠያቂ አድርጓል፡፡

ታሪካዊ የአልነጃሺ መስጊድ ሲወድም ከአክራሪው ሀይል በመደገፍ የጨፈሩ ጥቂት የእምነቱ ተከታዮችም አሁን በእነሱ መድረሱን በመጥቀስ የአል-ነጃሺ መስጊድ ሲወድም ድምፅ አለማሰማታቸው ትክክል እንዳልሆነ ተመስገን ገመቹ አስተያየታቸውን አስፍረዋል፡፡

ሃያ አንድ ሙስሊም ፆሞኞችን መገደላቸው ተከትሎ የመንግስት እና የአማራ ክልል የመገናኛ ብዙሃን ግርግሩን አታራግቡት በማለት ለተፈፀመው  ግድያ ማሳነሳቸው እውነትም እነዚህ ሰዎች   ስንት ሙስሊም ማህበረ-ሰብም ለመግደል አስበው ነበር በማለት የጠየቁም አልጠፉም፡፡

በመብራህቱ ይባልህ