……
የትግራይ ሰራዊት ዋና ኣዛዥ ታጋይ ታደሰ ወረደ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሰቆጣ በኩል ወደ ትግራይ ሰብሮ ለመግባት አዲስ ጥቃት መክፈቱን ኣስታወቁ፡፡
ከሶስት ቀን በፊት ወደ ኤርትራ የተሻገረው የፋሽስቱ ቅጥረኛ ሰራዊት ከኤርትራ ሰራዊት ግንባር በመፍጠር በኣዳያቦ፣ ኣስገለ እና ራማ የከባድ መሳርያ ድብደባ እያካሄደ መሆኑ ገልፀዋል፡፡
ዋና ኣዛዡ በመግለጫቸው የትግራይ ሰራዊት የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ለማረጋገጥ ከሚታገሉ የኢትዮጵያ ሃይሎች ጋር ተባብሮ እየሰራ መሆኑ ኣስታወቁ፡፡
የትግራይ ሰራዊት ከነሃሴ 18 ጀምሮ በደቡብ ግንባር የተቃጣበትን መጠነ ሰፊ ጥቃት በመመከት በወሰደው የፀረ ማጥቃት እርምጃ ግዙፍ የጠላት ሃይል በመደምሰስ አያሌ ኪሳራ ማድረሱን ገልፀዋል፡፡
የትግራይ ህዝብና መንግስት አሁንም ለሰላም ዝግጁ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።