Home ዜና የትግራይ ፕረዚደንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ ሚካኤል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት

የትግራይ ፕረዚደንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ ሚካኤል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት

439
0

የትግራይ ፕረዚደንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ ሚካኤል ለእስልምና ተከታዮች ፤ እንዲሁም የትግራይ ህዝብ ፤ ለጀግናው የትግራይ ሰራዊት እና በመላው አለም ለሚገኘው የትግራይ ዲያስፓራ እንኳን ለ1443 አመት የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ ብለዋል።

የመተጋገዝ እና ያለህን ተካፍላህ በዓልን የማሳላፍ የዳበረ ታሪካችንና ባህላችን በማጠናከር አንዳችን ከሌላችን ጋር ተደጋግፈንና ተጋግዘን ይህንን ግዜ ማለፍ እንዳለብን ለመጠቆም እወዳሎህ ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ ሚካኤል በዚህ አጋጣሚ በመደጋገፍ ረገድ ታላቅ ሚና እየተጫወታችሁ ላላችሁ ያለኝን አክብሮት እና አድናቆት ልገልፅ እወዳሎህ ብለዋል። ያለፈው ታሪካችን እንደሚያረጋግጠው እኛ ተጋሩ ቀጣይ ዕድላችን በጠንካራ ህብረታችን እና ውህደታችን የተመሰረተ መሆኑ የማያከራክር ጉዳይ ነው ያሉት የትግራይ ፕሬዝደንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ ሚካኤል ባለፉት 18 ወራት በነበረው የመራራ ትግል እና ድል ግዜ ዳግም የተረጋገጠ ጉዳይ ነው ብለዋል።

ከፅኑ ብሄራዊ ውህደታችንና ማህበራዊ ቅንጅታችን ፊት ሊቆም የሚችል ምድራዊ ሀይል እንደማይኖር ያለፉት 18 ወራት ትግላችንና ድላችን አረጋግጣል ያሉት የትግራይ መንግስት ፕሬዝደንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ ሚካኤል በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖረው የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ በአንድነት በመታገሉ አሁን ለደረስንበት ደረጃ ልንደርስ ችለናል ብለዋል።

አሁንም ቢሆን መፃኢ እድላችን በፈርጣማ ህብረታችንና ክንዳችን ላይ እንደሚመሰረት የትግራይ የተሟላ አርነት ለማረጋገጥ በምናካሂደው ትግል ዛሬም እንደ ወትሮው ህዝባዊ ትግላችንን እንድናጠናክር ጥሪዬን አቀርባሎህ ብለዋል።

ሚያዝያ 23/2014 ዓ/ም

Previous articleየአማራ ተስፋፊዎችም የትናንቱ ስህተታቸው በመድገም አገሪቷንና ህዝቧን ወደ ከፋ እልቂት እያስገቡዋት መሆኑ ሙህራን ተናገሩ፡፡
Next articleየኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ምስራቅ እዝ በፋሽስቱ ቡድን ሀይሎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡