የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ510 ሚልዮን ብር ድጋፍ ለትግራይ አበረከተ።
የትግራይ ግዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ የትግራይ ህዝብ ጠንካራ እና ታታሪ ህዝብ ነው ያሉ ሲሆን ትግራይ ሰሏምዋ ከተጠበቀላት በአጭር ግዜ ወደ ተሻለ ደረጃ የሚደርስ ህዝብ ነው ብለዋል።
ትግራይ በተከፈተባት ጦርነት ምክንያት በደረሰባት ውድመት መልሶ ለመገንባት የሁሉም ወገን ድጋፍ ይጠይቃል ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቡኩላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአይነት እና በጥሬ ገንዘብ የ510 ሚልየን ብር ድጋፍ አድርገዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአይነት እና የአይነት ድጋፉ የትግራይ ግዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ ተረክበዋል።