የፋሽሽቱ ቡድን ዛሬ መስከረም 4 2015 ዓ/ም ከጥዋቱ 2፡00 ኣከባቢ በመቀሌ ከተማ በመኖራያ ቤቶች በተፈፀመው የድሮን ድብደባ እስከ ኣሁን ኣስር ሰላማዊ ዜጎች መሞታቸው ታውቋል ፡፡ ከ 19 ሰላማዊ ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል ፡፡

ዛሬ የተፈፀመው የድሮን ድብደባ ሁለት ግዜ ሲሆን በመጀመርያ ድብደባ የተደጎዱ ሰዎች ለመርዳት በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ድጋሚ ድብደባ በማካሄዱ በሰውላይ የደረሰው ጉዳት እንዲያሻቅብ ኣድርጓል፡፡