Home ዜና ሀገር እንድትቀጥል ከተፈለገ ሁሉን ያካተተ ሀገራዊ ውይይትና ምክክር ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ተነገረ፡፡

ሀገር እንድትቀጥል ከተፈለገ ሁሉን ያካተተ ሀገራዊ ውይይትና ምክክር ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ተነገረ፡፡

643
0

የፋሽስቱ ቡድን ሃገሪቱን በመራበት ባለፉት አራት ዓመታት የኢትዮጵያ ህዝብ በአግባቡ ኑሮውን መምራት ያልቻለበት፣ ሰላምና መረጋጋት ጠፍቶ ሀገሪቱ የመፈራረስ አደጋ እንዲደቀንባት ማድረጉን ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው ተናገሩ፡፡

ኢትዮጵያ እንደሀገር እንድትቀጥል ከተፈለገ ሁሉን ያካተተ ሀገራዊ ውይይትና ምክክር ማድረግ ወሳኝ መሆኑንም አቶ ልደቱ ገልፀዋል፡፡

አራት ኪሎ በሰፈረው የፋሽስቱ ቡድን እየተመራች አራት አመታትን በቁልቁለት መንገድ እየተንገዳገደች የመፈራረስ ጫፍ ላይ የደረሰችው ኢትዮጵያ ባለፉት 27 አመታት ዲፕሎማሲን ጨምሮ በኢኮኖሚ በኢንዱስትሪ እና በግብርና ዘርፎች በእድገት ጎዳና ላይ የነበረች ቢሆንም አሁን ላይ ግን ያንሁሉ ህልም ሆኗል፡፡

በደካማ የፋሽስቱ ቡድን 4 አመታት የአመራር ጉዞም የኢትዮጵያ ህዝብ በአግባቡ ኑሮውን መምራት የማይችልበት ሰላምና መረጋጋት የራቀበት ጊዜ እንደነበር ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው ይናገራሉ፡፡ ከዚህ አልፎም አመራሩ የሃገሪቱን ሁለንተናዊ ቀውስ ሲያባብስ እንጂ ለማስተካከል አዎንታዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ አልታየም ብለዋል፡፡

የፋሽስቱ ቡድን  በትግራይ ህዝብ ላይ ባወጀው ጦርነት የባእድ ሀገር ሰራዊት እንደፈለገው እንዲፈነጭ በማድረግ የሀገሪቱን ሉአላዊነት አስደፍሯል የሚሉት አቶ ልደቱ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈፀሙንም ያነሳሉ፡፡

የፋሽስቱ ቡድን መሪ #አብይ አሕመድ በያዘው የውድቀት መንገድ እስከቀጠለ ድረስ የሀገሪቱ ህልውናም እጅግ አስጊ እንደሚያደርገው ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ይላሉ ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው ኢትዮጵያ እንደሀገር እንድትቀጥል ከተፈለገ ሁሉን ያካተተ ሀገራዊ ውይይትና ምክክር ማድረግ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ዊንታ ዘላለም                          

Previous articleሞያሌ ከተማ ሞያሌ ግጭት መቀስቀስ
Next articleየማህበራዊ የትስስር ገጾች ውሎ