Home ዜና ለዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መርማሪ ኮሚሽን የኢትዮጵያ መንግስት እንዲተባባር የአውሮፓ...

ለዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መርማሪ ኮሚሽን የኢትዮጵያ መንግስት እንዲተባባር የአውሮፓ ህብረት ጠየቀ፡፡

797
0


የተባበሩት
መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ላቋቀመው ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መርማሪ ኮሚሽን የኢትዮጵያ መንግስት እንዲተባባር የአውሮፓ ህብረት ጠየቀ፡፡ የተባባሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት በትግራይ ህዘብ ላይ የተፈጸሙትን የጦር ወንጆሎች እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በገለልተኛ አካል ተጣርቶ አጥፊዎችን እንዲጠየቁ ለማድረግ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መርማሪ ኮሚሽን ማቋቋሙን ይታወሳል፡፡

የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ መንግስትን ለዓለም አቀፉ መርማሪ ኮሚሽን ሙሉ ትብብር እንዲያደርግለት የጠየቀው Amnesty international & human rights watch በጥምረት በትግራይ ምዕራባዊ ዞን የተፈጸሙትን የጦር ወንጀሎች፣በሰብአዊነት ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎችና የዘር ማጽዳት ዘግናኝ ግፎች መካሄዳቸውን በምርመራ ውጤታቸው ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው፡፡ህብረቱ ባወጣው መግለጫ፣በትግራይ ምዕራባዊ ዞን በሰላማዊያን የትግራይ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለው መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ግፎችን አስመልክቶ የሰብአዊ መብት ተሟጓች ድርጅቶቹ ያወጡት ሪፖርት የአውሮፓ ህብረትን እጅግ አስደንግጦታል ብሏል፡፡

ገለልተኛ የሆነው እና በተባባሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት የተቀቋመው አጣሪ ኮሚሽንም መረጃዎችን ይፋ በማድረግ ኃላፊነትና ተጠያቂነት በማስፈን ለተጎጆዎች ፍትህን ለማምጣት በአፋጣኝ መስራት ያስፈልጋል ብሏል፡፡ምርመራዎቹ በአስቸኳይ እንዲጀመሩ የኢትዮጵያ መንግስት ሙሉ በሙሉ እንዲተባባር የአውሮፓ ህብረት ጥሪውን በድጋሚ ያቀርባል ሲልም ነው በመግለጫው ላይ ያስታወቀው፡፡

ከአውሮፓ ህብረት በተጨማሪም የአሜሪካ መንግስትም የሰብአዊ መብት ተሟጓቾቹ በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ላይ ተፈጸመ ያሏዋቸው ጥሰቶችን አስመልክቶ ባወገዘበት መግለጫው የኢትዮጵያ መንግስት ለተቋቋመው ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን ትብብር እንዲያደርግ ጠይቋል፣፣የአውሮፓ ህብረት በአምስተኛው የተባባሩት መንግስታት ኮሚቴ ተይዞ የነበረው የዓለም አቀፉ አጣሪ ኮሚሽን የበጀት ውይይት መዘግየት እንዳሳዘነውም ገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ የተመድ ሰብአዊ መብቶች ምክርቤት ጉባኤ ላቋቋመው አዲሱ የሰብአዊ መብቶች መርማሪ ኮሚሽን በጀት እንዳይመደብ ለጠቅላላው ጉባኤ ሃሳብ አቅርባ የነበረ ቢሆንም የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ኢትዮጵያ ያቀረበችው የውሳኔ ሃሳብ በአብላጫ ድምጽ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል፡፡አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዎች በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ያካሄዱት ምርመራ እና በጥምረት ይፋ ባደረጉት ሪፖርት ላይ ተስፋፊ የአማራ ሚሊሻ ፣ ፋኖ ታጣቂዎች እና በወቅቱ በስፍራው ተመድበው በነበሩ ጊዝያዊ ባለስልጣናት የጦር ወንጀሎችን፣ በሰብአዊ መብት ላይ የሚፈጸም ወንጀሎች እና የዘር ማጽዳት ወንጀሎችን ከጦርነቱ መባቻ ጀምሮ ሲፈጽሙ መቆየታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በሁሉቱም የሰብአዊ መብት ተሟጓቾች ጥምረት ተጠንቶ የቀረበውን ዘግናኝ የጦር ወንጆሎች፣ በትግራይ ተወላጆች ላይ የዘር ማጽዳት ወንጀሎች እና ሎሎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የኢትዮጵያ መንግስት አልቀበለውም በማለት አጣጥሎታል፡፡

አማረ ኢታይ

Previous articleሰብአዊ እርዳታ ወደ ትግራይ ለማስገባት መቸገሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡
Next articleየኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ትግል በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች ድል መቀናጀቱ ተነገረ፡፡