Home ዜና ለጋሽ ድርጅቶች እጃቸውን ካልዘረጉ በአፍሪካ ቀንድ በሚልዮኖችን   በረሃብ ሳቢያ በሞት አፋፍ ላይ...

ለጋሽ ድርጅቶች እጃቸውን ካልዘረጉ በአፍሪካ ቀንድ በሚልዮኖችን   በረሃብ ሳቢያ በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኙ የተ.መ.ድ አስጠነቀቀ።

842
0

Zaire የተባለ ድረ ገፅ እንደዘገበው የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦቱ ሩስያ በዩክሬን ላይ በከፈተችው ጦርነት ሳቢያ ተስተጓጉላል፤ የተ.መ.ድ ሰብአዊ ጉዳዮች ሃላፊ ማርቲን ግሪፍትስ በዓላማችን ከአፍሪካ ቀንድና ሳህል አካባቢ የበለጠ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ህዝቦች የሉም ብለዋል። የአካባቢው ህዝቦች ባልፈጠሩት የአየር ንብረት ለውጥ መዛባት ሳቢያ ለስቃይ እየተዳረጉ እንደሆነ ያመለከቱት ሃላፊው ችግሩ የአየር ንብረት ለውጥ መዛባት ውጤት መሆኑን አስረድተዋል።

በረሃቡ ምክንያት 35 ሚልዮን ህዝቦች በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኙ ኬንያ  ሲጐበኙ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

አሁን ድርቅ ያጋጠመው አፍሪካ ቀንድ አካባቢ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ኬንያን የሚያጠቃልል ሲሆን 5000 ኪሎ ሜትር ቁመትና 1000 ስፋት ያለው ከስሃራ በረሃ ወደ ደቡብ ያለው የሳሕል አካባቢ ከአትላንቲክ ባህር እስከ ቀይ ባህር ድረስ የሚሸፍን ሲሆን ቡርኪናፋሶ፣ ቻድ፣ ማሊ እና ናይጀሪያ ክፉኛ የተጠቁ አገሮች ናቸው ተብሏል።

በአሁኑ ሰዓት አስፈላጊውን እርዳታ ካልቀረበ የነዚህ 35 ሚሊዮን ህይወት ለማዳን የሚደረገውን ርብርብ ከባድ እንደሚያደርገው ማርቲን ግሪፍትስ አስጠነቅቀዋል።

ሩስያ በዩክሬን ላይ የከፈተቸው ጦርነት በአፍሪካ ላይ ተፅእኖ መፍጠሩ ያመለከተው ዘገባው ለዩክሬን እየቀረበ ካለው እርዳታ አንፃር አስቸኳይ ለአፍሪካ  የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦቱ የዘገየና በቂ አይደለም ተብሏል።

በአፍሪካ ያንዥበበው የረሃብ አደጋ ከዩክሬይንና ሩስያ ይመጣ የነበረው የእህል አቅርቦት  በመቋረጡ ምክንያት በምግብ ዋጋ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ማስከተሉን ዘገባው ያስረዳል።

እርዳታ ለጋሽ ድርጅቶች በአፍሪካ ቀንድና ሳህል አካባቢ ከ40 ዓመት ወዲህ ያጋጠመው የድርቅ አደጋ የብዙዎችን ህይወት ከመቅጠፉ በፊት ሊደርሱለት እንደሚገባ ግሪፍትስ አሳስበዋል፤ ለከፍተኛ ረሃብ የተጋለጡት ህዝቦች ቁጥር   ሊጨምር እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል።  

 ኩኖም ቀለሙ    

Previous articleዘንድሮ የሚከበረዉን የንቦች ቀን በትግራይ ቀኑን ታስቦ እንዲዉል የሚያስችል ሁኔታ አለመኖሩን ተገለፀ፡፡  
Next articleየትግራይ ውጭ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት መግለጫ