Home ዜና ሩሲያና ቻይና ፋሽስቱ በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጠረውን የረሃብ ቸነፈር አፋጣኝ መፍትሄ እንዳያገኝ...

ሩሲያና ቻይና ፋሽስቱ በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጠረውን የረሃብ ቸነፈር አፋጣኝ መፍትሄ እንዳያገኝ ማደናቀፋቸው ማርክ ሎውኮክ ገለፁ፡፡

646
0

ሩሲያና ቻይና ፋሽስቱ በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጠረውን የረሃብ ቸነፈር አፋጣኝ መፍትሄ እንዳያገኝ ማደናቀፋቸው ማርክ ሎውኮክ ገለፁ፡፡

——

በተባባሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩ ማርክ ሎውኮክ ሩሲያና ቻይና ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጠረውን የረሃብ ቸነፈር አፋጣኝ መፍትሄ እንዳያገኝ ማጨናገፋቸው አጋለጡ፡፡

የቀድሞ የተባባሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮችና የአስቸኳይ ድጋፍ አስተባባሪ ማርክ ሎውኮክ ከዴቬክስ ድረ ገጽ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳመለከቱት ዓለም አቀፍ የትግራይ የረሃብ ቸነፈር አዋጅን እንዲታወጅ በተባባሩት መንግስታት የተጠራው ስብሰባ ላይ እንዲጨናገፍ ሩሲያና ቻይና አሉታዊ ሚና ተጫውቷዋል፡፡

እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ በትግራይ ህዝብ ላይ ያጋጠመው የረሃብ ቸነፈር በግልጽ አልተነገረለም ያሉት ሎውኮክ፣ በዚህም ምክንያት ግማሽ ሚሊዮን ያህል የትግራይ ህጻናት በተመጣጠነ የምግብ እጥረት ሳቢያ ችግር ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በትግራይ ህዝብ ላይ ያጋጠመው የረሃብ ቸነፈር በጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ አስቸኳይ ትኩረት ከተደረገበት  ህዝቡ የደረሰበትን አደጋ ትኩረት ያገኛል፤ እንዲሁም በፋሽስቱ ቡድን ላይ የፖለቲካ ግፊት በመፍጠር በርካታ የሰብአዊ ድጋፍ ይደረጋል የሚል እምነት እንዳላቸው ሎውኮክ አመልክተዋል፡፡

ችግሩን በዘገየ ቁጥር በትግራይ ሴቶችና ህጻናት ላይ ስቃዩን ይበረታል ያሉት ሎውኮክ፣ ከሩሲያና ቻይና ተሳትፎ ውጪና ከተወሰኑ የአፍሪካ ሃገራት ቁጣ በስተቀር ሊካሄድ የታቀደው የምክክር ስብሰባ እንዲካሄድ በአብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሃገራት ፍላጎት እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

በማርክ ሎውኮክ አስተያየት ላይ፣ ሩሲያና ቻይና አስተያያት መስጠት መቆጠባቸው  የዴቬክስ ድረ ገጽ አመልክቷል፡፡

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ የረሃብ ቸነፈር መከሰቱን እያወቀ ነገር ግን ዓለም አቀፍ የረሃብ ቸነፈር አዋጁን ተግባራዊ እንዳይሆን በማዘግየትና ሁኔታውም ቸነፈር መሰል ሁኔታ በማለት ትኩረት እንዳይስብ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑንም ነው ድረ ገጹ የገለጸው፡፡

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ አያሌ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን መፈፀሙ የዓለም ህብረተ-ሰብ እየተገነዘበ  መምጣቱይ እና የሰብአዊ ድጋፍ ያለገደብ እንዲገባ ግፊት እያደረገ መሆኑን ያስታወሰው ድረ ገጹ፣ ሩሲያና ቻይና በአንጻሩ የህዝቡን ችግር የኢትዮጵያ የውስጥ ችግር ነው በማለት አሉታዊ ሚና እየተጫወቱ መሆናቸውን ሎውኮክ አስታውሰዋል፤ ሁለቱ አገራት የያዙት አቋም ፋሽስቱ የአብይ ቡድን የትግራይ ጦርነት የህግ የማስከበር ዘመቻ ነው በማለት ወንጀሉን እንዲቀጥልበት እንዳበረታታው ገልጸዋል፡፡   

በትግራይ ህዝብ ላይ የደረሰው የረሃብ ቸነፈር ዓለም አቀፍ አዋጅ መጨናገፉ አያሌ ሰዎች በረሃብ ቸነፈሩ  በጅምላ እንዲያልቁ አድርጓል ያሉት ሎውኮክ፣ አዋጁ በወቅቱ ተግባራዊ ቢሆን ኖሮ ደቡብ ሱዳን፣ የመን፣ ሶማሊያ፣ እና ናጀሪያ ከዚህ ቀደም አጋጥሞ የነበረውን የረሃብ ቸነፈር ለመቀልበስ በታቻለ ነበር ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ራሱ የፈጠረው የረሃብ ቸነፈር የትግራይ ተወላጆች ከምድረ ገጽ እንዲጠፉ እንደ አንድ ስልት እየተጠቀመበት እንደሚገኝ ያስታወሱት ሎውኮክ፣ የትግራይ ህዝብም ህይወቱን ለማቆየት እና ላለመጥፋት ያልተለመዱ እጽዋቶችን እንዲመገብ እንደተገደደም አመልክተዋል፣፣

አማረ ኢታይ

Previous articleየትግራይ ህዝብ ፀረ ባርነት የነፃነት ተጋድሎ በትውልድ ቅብብሎሽ እየቀጠለ መሆኑ የትግራይ ሴ/  ኮማንድ አባል አቶ ጌታቸው
Next articleየተጎጋ ጥቃት ሰለባዎች  የሰማእታት ቀን አንደኛ አመት ተከበረ ፡፡