Home ዜና በማዳበርያ ዋጋ መናር̎ ምክንያት መሬታችን ምንም አዝርዕት ሳይዘራበት ሊከርም ይችላል ሲሉ አርሳደሮች...

በማዳበርያ ዋጋ መናር̎ ምክንያት መሬታችን ምንም አዝርዕት ሳይዘራበት ሊከርም ይችላል ሲሉ አርሳደሮች ስጋታቸው ገለፁ

567
0

በማዳበርያ ዋጋ መናር̎ ምክንያት መሬታችን ምንም አዝርዕት ሳይዘራበት ሊከርም ይችላል ሲሉ አርሳደሮች ስጋታቸው ገለፁ፡፡ የአፈር ማደበርያ ከባለፈው ኣመት ጋር ሲነፃፀር ዘንድሮ ከ150 በመቶ በላይ ጨምሯል ፡፡ ይህም ለአርሶአደሩ ራስ ምታት ሆኗል ሲል BBC በዘገባው አስነብባል፡፡

መሬታችን ጦም ሊያድር ይችላል ሲሉ አርሶአደሮች ገልፀዋል ሲል ፅሁፉን የጀመረው የBBC ሃተታ በፅሁፉም ባለፈው ዓመት 1700 ብር ይገዛ የነበረው ማዳበርያ ዘንድሮ ዋጋው ከእጥፍ በላይ ጨምሮ 4200 ብር መግባቱን ገልፃል፡፡

BBC ያነጋገራቸው ኣርሳደሮች ኣንዱ የሆኑት ኣርሶኣደር ጌቱ የዋጋ ንረቱ በምርታቸው ላይ ከፍተኛ ጫና እንዳሳደረባቸው በመግለፅ ለማዳበርያ 25 ሺ ብር አወጣለው ብየ ኣቅጄ ነበር ቢሆንም ግን ባለው የዋጋ ንረት አሁን በእጥፍ አድጎ ከ50 ሺ ብር በልጧል ታድያ እንዴት አድርጌ እዘራለው ሲሉም ይጠይቃሉ፡፡

የዋጋ ንረቱ ተከትሎም ማዳበርያ የማይፈልጉ እና ዋጋ የማያወጡ ሰብሎች መዝራት እንደ አንድ ለመውሰድ ኣስገስድዶናል ሲሉም ሃሳባቸውን ገልፀዋል፡፡ አርሳደር ጌቱ ኣክለውም እስካሁን ኣንድም ማዳበርያ ኣለመግዛታቸውንና ለበጋ መስኖ ቀደም ብሎ ከሰው ተበድሬ የዘራሁትንም እንዴት እንደምከፍል ጭንቅ ሆነብኛል በማለት ያሉበትን ኣስከፊ ሁኔታ ተናግረዋል፡፡ ሌላኛው አርሳደር ሹመትም በተመሳሳይ መልኩ የመንደራችን የማለዳና የምሽት ወሬ ስለማዳበርያ ሆናል ብለዋል፡፡

መሬታችን በአዝርዕት ለመሸፈን ቢያንስ ኩንታል NPS እና አራት ኩንታል ዩርያ ማዳበርያ እንደሚያስፈልጋቸው የገለፁት አርሳደር ሹመት ይህንን ለመግዛትም አቅማቸው እንደማይፈቅድ በመግለፅ ይህን ተከትሎም መፍትሄ ካልተሰጠ ምንም አይነት ምርት ማምረት እንደማይችሉም BBC ባሰፈረው ሃተታ ተጠቅሷል፡፡

እኔ ደሃ አርሶአደር ነኝ በተባለው ዋጋ ገዝቼ ማምረት አልችልም ያሉት አርሶአደር ሹመት ልጆቼ የሚቆርጡት እሸት እንዳያጡ ጥቂት በቆሎ እዘራ እነደሆን እንጂ ኣሁን ባለው የዋጋ መናር እማመርተው ነገር የለምም ብለዋል፡፡መአዛ መኮነን

Previous articleኢትዮጵያ በትግራይ ለተፈጸመው ጀኖሳይድ ማስረጃ የማጥፋት ዘመቻ
Next articleየማህበራዊ ሚድያ ውሎ