Home ዜና በምዕራብ ትግራይ የዘር ማፅዳት፣ የጦር ወንጀሎች እና በሰብአዊነት ላይ ወንጀል መፈፀሙ ተረጋገጠ

በምዕራብ ትግራይ የዘር ማፅዳት፣ የጦር ወንጀሎች እና በሰብአዊነት ላይ ወንጀል መፈፀሙ ተረጋገጠ

634
0

“ከዚች ምድር እናጠፋችኋለን “አምኒስቲ ኢንተርናሽል በምዕራብ ትግራይ የዘር ማፅዳት፣ የጦር ወንጀሎች እና በሰብአዊነት ላይ ወንጀል መፈፀሙ ያረጋገጠበት ሪፓርት የሰጠው ርእስ ነው።በትግራይ ህዝብ ላይ የተከፈተው የዘር ማጥፋት (የጄኖሳይድ ወንጀል) ጦርነት ተከትሎ ፣ የአማራ ተስፋፊ ሃይሎች ከቅጥረኛው የኤርትራና እና የኢትዮጵያ ወታደሮች ጋር በመተባበር በምዕራብ ትግራይ የዘር ማፅዳት (Ethnic Cleansing)፣ የጦር ወንጄሎች (War Crimes) እና በሰብኣዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጄል (Crime against Humanity) ድርጊቶችን መፈፀማቸው የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጏች ድርጅቶች አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሁዩማን ራይትስ ዎች ባካሄዱት ጥናት ማረጋገጣቸው በሪፓርታቸው ይፋ አድረጉ ::

ፋኖ የሚባለው ዘራፊ፣ ጨፍጫፊ ቡድን እና ሌሎች የአማራ ተስፋፊ እና ታጣቂዎች ስልክና ኢንተርኔት እንዲሁም ሁሉም የመገናኛ አውታሮች ዘግተው በምዕራብ ትግራይ ህዝብ ላይ የፈፀሙት አረሜኒያዊና ባርባራዊ ወንጀሎች በአለም አቀፍ ደረጃ በእነዚህ ተቋማት ሲጋለጥ የመጀመሪያ ነው ማለት ይቻላል ::

የአማራ ክልል ባለስልጣናት በምዕራብ ትግራይ በትግራይ ተወላጆች ላይ የጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት የሚፈጸሙ ወንጀሎች ፈጽመዋል ተባለየአማራ ክልል የጸጥታ ሃይሎች እና የሲቪል ባለስልጣናት በኢትዮጵያ ምዕራብ ትግራይ ዞን ከህዳር 2020 ጀምሮ በትግራይ ተወላጆች ላይ የጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ፈፅመዋል ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂውማን ራይትስ ዎች ዛሬ ባወጡት አዲስ ዘገባ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ባለስልጣናትም ብሔርን የማጽዳት ዘመቻን በስፋት በመደበቅ የክልሉን ተደራሽነት እና ገለልተኛ ምርመራን በመገደብ ከፍተኛ ድርሻ ወስዷል በማለት ሪፓርቱ ከሰዋል።“ከዚች ምድር እናጠፋችኋለን” ወይም “We Will Erase You From This Land’: Crimes Against Humanity and Ethnic Cleansing in Ethiopia’s Western Tigray Zone” ተብሎ የተሰይመው ባለ 240 ገጽ ሪፓርት በኢትዮጵያ ምዕራብ ትግራይ ዞን በሰው ልጆች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች እና ብሄር መሰረት ያደረጉ ወንጀሎች፣ በምእራብ ትግራይ አዲስ የተሾሙ ባለስልጣናት እና የአማራ ክልል የጸጥታ ሃይሎች በታማኝነት ሊሳተፉ የሚችሉበትን ሁኔታ ይዘረዝራል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ሃይሎች ዛቻ፣ ህገወጥ ግድያ፣ ጾታዊ ጥቃት፣ የጅምላ እስር፣ ዘረፋ፣ የግዳጅ ዝውውር እና ሰብአዊ እርዳታ በመከልከል በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆችን ከመኖሪያ ቤታቸው በስልት ተባረዋል ይላል ሪፓርቱ። እነዚህ በትግራይ ሲቪል ህዝብ ላይ የተስፋፉት ስልታዊ ጥቃቶች በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች እና የጦር ወንጀሎች ናቸው። የሂዩማን ራይትስ ዎች ስራ አስፈፃሚ ኬኔት ሮት “ከህዳር 2020 ጀምሮ የአማራ ባለስልጣናት እና የጸጥታ ሃይሎች በምዕራብ ትግራይ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችን ከመኖሪያ ቤታቸው ለማስወጣት ያላሰለሰ የዘር ማጽዳት ዘመቻ አካሂደዋል።” በማለት የአማራ ክልል ባለስልጣናትን ተሳትፎ መጠን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ እና ክልላዊ አጋሮች ምላሽ በምዕራብ ትግራይ እየተፈጸመ ያለውን የወንጀል አስከፊነት ማንጸባረቅ አልቻለም ያሉት ደግሞ አግነስ ካላማርድ፣ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዋና ጸሃፊ ናቸው።ይህ በትግራይ ህዝብ ላይ በ21 ኛው ክ/ ዘመን ይፈፀማል ተብሎ የማይገመተው የጄኖሳይድ ተግባር ተጋልጦ እውን እንዲሆን ደግሞ ከፍተኛ ትግል ሲያካሂዱ የነበሩት ሁሉም ወገኖች ክብር ይገባቸዋል የሚያስብል ሁነት ነው ::

የአማራ ተስፋፊ ሃይል በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ማፅዳትና የዘር ማጥፋት የፈፀመ ሃይል መሆኑ በተደጋጋሚ ሲነገር የቆየ ሀቅ ነው :: አሁንም እነዚህ ግፈኞች በሰሩት አረሜኒያዊ የጄኖሳይድ ተግባር ከተጠያቂነት እንዳያመልጡ ሁሉም ትግራዋይ እና የትግራይ ህዝብ ወዳጅ ትግሉ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል መልእክታችን ነው።

ትግራይ ትስዕር!

ሙሉውን “ከዚች ምድር እናጠፋችኋለን” የተሰኘውን ሙሉ ሪፓርት ለማንበብ ይኸንን ሊንክ ይጫኑ

Previous articleየማህበራዊ የትስስር ገጾች ውሎ
Next articleየትግራይ ህፃናት ድምፅ