Home ዜና በሱዳን የስደተኞች መጠልያ ውስጥ የሚገኙት የትግራይ ተወላጆች በተከሰተው ረሀብ   የትግራይ ዳያስፖራ ሊደርሱልን...

በሱዳን የስደተኞች መጠልያ ውስጥ የሚገኙት የትግራይ ተወላጆች በተከሰተው ረሀብ   የትግራይ ዳያስፖራ ሊደርሱልን ይገባል አሉ፡፡

940
0

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለትግራይ ተወላጅ ስደተኞች የሚሰጠውን ድጋፍ በግማሽ ለመቀነስ የያዘውን እቅድ ተከትሎ ስደተኞች ለከፍተኛ የረሀብ አደጋ ተጋልጠዋል፡፡

ከትግራይ በተስፋፊ ሀይሎች የሚደርሰውን ግፍና ሰቆቃ ሽሽት የመኖርያ ቀዬዋን ትታ  በሱዳን ዑምራኮባ የስደተኞች መጠልያ የምትገኘው እናት ወ/ሮ አለም ኪዳነ አራት ልጆቿን ብቻዋን ነው የምታሳድገው፤ ይህች እናት በትግራይ በነበረችበት ወቅት ልጆቿን በአቅሟ የፈለጉትን እንዲያገኙ ስታደርግ ብትቆይም አሁን ግን አልቻለችም፤ በስደተኞች መጠለያ ውስጥ የሚሰጠው እርዳታ በቂ ባለመሆኑም አሁን ላይ ልጆችዋ በረሀብ ታመው እንደሚገኙ ትገልፃለች፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከስልሳ ሺህ በላይ ለሚሆኑ የትግራይ ተወላጅ ስደተኞች ሲሰጠው የነበሩውን ወርሀዊ እርዳታ በግማሽ ለመቀነስ አቅዷል፤ ይህ ደግሞ ለወ/ሮ አለም ከፍተኛ ስጋት ደቅኖባት ይገኛል፡፡

ሌላው ቀርቶ መኖርያ ቤታቸው እንኳን በዝናብ ፈርሷል፤ ግን ለመሆኑ ለአንድ ሰው በሚሰጠው 14 ኪሎ ማሽላ እንዴት ነበር ህይወትን ሲገፉ የነበሩት።

በሱዳን ዑምራኮባ የስደተኞች መጠልያ የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ ስደተኞች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የወሰነው ውሳኔ የሞት ፍርድ ነው ሲሉ ይገልፁታል፡፡ 

በመጨረሻም የትግራይ ተወላጅ ዳያስፖራዎች እንዲሁም የአለም ማህበረ-ሰብ በረሀብ ከማለቃችን በፊት ሊደርሱልን ይገባል ብለዋል፡፡

በዊንታ ዘላለም 

Previous articleየትግራይ መንግስት መግለጫ
Next articleየትግራይ ተወላጆችን የሚታጎሩባት እና የሚሰቃዩባት በአዲስአበባ  የትግራይ ተወላጅ ሴት አትሌቶች በዓለም መድረክ ያስመዘገቡትን አንፀባራቂ ድል ምክንያት ደስታዋን ስትገልፅ ውላለች።