Home ዜና በትግራይ ህዝብ ላይ በተፈጠረው ሰው ሰራሽ ርሃብ ምክንያት አንዲት የአርባ ቀናት እድሜ...

በትግራይ ህዝብ ላይ በተፈጠረው ሰው ሰራሽ ርሃብ ምክንያት አንዲት የአርባ ቀናት እድሜ ያለውን ህፃን እናት ህይወትዋ ማለፉ ተገለፀ፡፡

1082
0
ወ/ሮ ፀጋ

——- 

እናቱ በርሃብ ምክንያት በሞት የተለየችው የአርባ ቀናት እድሜ ያለውን ህፃን በበኩሉ በምግብ እጦት ሳብያ በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ እንደሚገኝ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ የቤተሰብ አባላት ገልፀዋል፡፡

በዓዲግራት ከተማ እስከ  መጋቢት ወር 2014 ዓ/ም በርሃብና በመድሃኒት እጦት  ምክንያት  የበርካታ ሰዎች ህይዎት ማለፉን የከተማዋ  የሰራተኞች ጉዳይና የህብረተ-ሰብ ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ዘርፍ ፅህፈት ቤት አስታውቋል ፡፡

ወ/ሮ ፀጋና ወ/ሮ ስእላ ፋሽስታውያን  ወራሪ ሃይሎች  በትግራይ ህዝብ ላይ ካወጁት የጀኖሳይድ ጦርነት  ለማምለጥ  ከሑመራ እና ዛላንበሳ  ከተሞች ወደ ዓዲግራት ከተማ  ተፈናቅለው በተፈናቃዮች ጊዚያዊ መጠለያ ጣብያ ላይ  ነበር የተዋወቁት፡፡

ወ/ሮ ስእላ

ወ/ሮ ስእላ እንደሚገልፁት  በወቅቱ ነብሰ  ጡር የነበረች ወ/ሮ ፀጋን ዘመዳቸው መጠልያ ይሆናቸው ወደ ሰጧቸው የመኖረያ ቤት ወስደው አዋልደዋታል፡፡ ሆኖም ለአራስ የሚዘጋጅ ምግብ ይቅርና ለአንድ ለሊት የሚሆን የሚላስ የሚቀመስ ምግብ ባለ መኖሩ  በርሃብ ምክንያት የወ/ሮ ፀጋ ህይወት እንዳለፈ  ይናገራሉ ፡፡      

የወ/ሮ ፀጋ ባለቤት አቶ ደስታ ግርማይ  ፋሽስታዊያን በፈጠሩት ሰው ሰራሽ ርሃብ ምክንያት ባለቤቱ የ 40 ቀን እድሜ ያለው ጨቅላ ትታ  ህይዎትዋ  በማለፉ በችግር ላይ ችግር ተደራርቦበት ሊሸከመው የማይችለውን ከባድ ችግር ውስጥ እንደሚገኝ ይናገራል፡፡

ወ/ሮ ፀጋ ፋሽስታዊያን  በፈጠሩት ሰው ሰራሽ ርሃብ ምክንያት ገና አይታ ያልጠገበችውን የ40 ቀን ህፃን ትታ ህይወትዋ እንዳለፈ የምትገልፀው  የወ/ሮ ፀጋ ጓደኛ  የሆነችው ሃረግ ህፃኑ በአሁኑ ወቅት  ወ/ሮ ስእላ  እጅ ላይ ቢሆንም  ለህፃኑ የሚሆን ምግብ ግን ማግኘት እንዳልቻሉ  ትግልፃለች፡፡

ፍሬሂወት ተ/መድህን

Previous articleበትግራይ በርሃብ ምክንያት ከ200 000 በላይ ህፃናት እንደሞቱ  ተገለፀ፡፡
Next articleየትግራይ መንግስት ፕሬዝዳንት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል ከፋሽስቱ ቡድን ጋር እስካሁን የተካሄደ ድርድር እንደሌለ ተናገሩ፡፡