Home ዜና በትግራይ ላይ የተፈፀመው የቤተ እምነት ውድመት አወደ-ርእይ ማሳያ—

በትግራይ ላይ የተፈፀመው የቤተ እምነት ውድመት አወደ-ርእይ ማሳያ—

1021
0

በትግራይ ህዝብ እንዲሁም በእምነት ተቋማቱና ቅርሶቹ የደረሰው አስነዋሪ ጭፍጨፋና ውድመት የኢትዮጵያ ህዝብ ሆነ ዓለም አቀፉ ማህበረ-ሰብ በራሱ ላይ የተፈፀመ ያክል ግንዛቤ ሊኖረው እንደሚገባ የሃይማኖት አባቶች ገለፁ፡፡

የትግራይ ህዝብ ጠላቶች በትግራይ ህዝብና በሃይማኖታዊ ቅርሶቹ ላይ የፈፀሙትን ጀኖሳይድ ወንጀል የሚያሳይ አውደ-ርኢ በመካነ ሰማእት ቅዱስ ጊዮወርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተካሄደ፡፡

በመቐለ ከተማ መካነ ሰማእት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰበካ ጉባኤ አዘጋጅነት ፋሸስቱ የአብይ ቡድንና የአምባገነኑ የኢሳያስ ቅጥረኛና ነውረኛ ወታደሮች በትግራይ ህዝብና በሃይማኖታዊ ቅርሶቹ ላይ የፈፀሙትና እየፈፀሙት ያለው ጀኖሳይድ የሚያሳይ አውደ-ርኢ ተካሄዷል፡፡ አወደ-ርእዩ በትግራይ ህዝብ እንዲሁም በእምነት ተቋማቱና ቅርሶቹ የደረሰው አስነዋሪ ጭፍጨፋና ውድመት የኢትዮጵያ ህዝብ ሆነ ዓለም አቀፉ ማህበረ-ሰብ በራሱ ላይ የተፈፀመ ያክል ግንዛቤ እንዲኖረው አላማ ያደረገ አወደ-ርእይ እንደሆነ የሃይማኖት አባቶች ገልፀዋል፡፡

በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመው አረመኔያዊ ጭፍጨፋ የሃይማኖታዊ ቅርሶችና ቤተ እምነቶች ውድመት ሆን ተብሎ እንደተፈፀመ የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ የዓለም ማህበረ-ሰብ ሊዘናጋ አይገባውም ያሉት እነዚህ የሃይማኖት አባቶች በትግራይ ህዝብና በእምነቱ እና በታሪኩ ላይ እየደረሰ ያለውን የጀኖሳይድ ወንጀል እንዲቆም ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ በትግራይ በተካሄደው የጀኖሳይድ ጦርነት አብያተ እምነቶች የትግራይ ህዝብ ታሪክና ስልጣኔ የያዙ ቅርሶች ሆን ተብለው በወራሪዎች መውደሙ ይታወቃል፡፡

በሄለን ሃፍቱ

Previous articleየፋሽስቱ ቡድን ያቀረበው ክስ መሰረት እንደሌለው የትግራይ የውጭ ጉዳይ ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡
Next articleአለም አቀፍ የተጋሩ ባለሙያዎችና ምሁራን የአቋም መግለጫ