Home ዜና በትግራይ በአበርገለ የጭላ ወረዳ  ነዋሪዎች አባሰንጋ እየተባለ የሚጠራው  የእንስሳት በሽታ  ጉዳት እያደረሰ...

በትግራይ በአበርገለ የጭላ ወረዳ  ነዋሪዎች አባሰንጋ እየተባለ የሚጠራው  የእንስሳት በሽታ  ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ተገለፀ፡፡

1294
0

የፋሽስቱ ቡድን ወደ ትግራይ ምንም ኣይነት መድሃኒት እንዳይገባ መከልከሉ ተከትሎ በተለምዶ የደስታ ወይንም አባሰንጋ እየተባለ የሚጠራው  የእንስሳት በሽታ በአበርገለ የጭላ ወረዳ  ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ተገለፀ፡፡

በወረዳዋ የሚገኙ እንስሳት የተለመደው ክትባት ለሦስት ዓመታት ባለመሰጠቱ  እስካሁን ከሰባት ሺ በላይ እንስሳት በበሽታው መሞታቸውም ተጠቅሳል፡፡

ይህ የምንመለከተው ህፃን  ባላሰበው መንገድ የዓይን ህመም የደረሰበት  ነው ፡፡

ይህ ክስተት ያጋጠመው በአበርገለ የጭላ ወረዳ ሲሆን ህጻኑ አሁን ላይ በየጭላ መለስተኛ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት ይገኛል፡፡ የህፃኑ ወላጅ ኣባት ኣቶ ጌራ እንደሚሉት ከሆነ የደስታ በሽታ ወይም በኣባሰንጋ ተጠቅታ የሞተች ላም መብላቱንና ስጋው በልቶ ከ3 ቀናት በኋላ ኣይኑ ላይ እብጠት እንደታየበት ይናገራሉ፡፡

በየጭላ መለስተኛ ሆስፒታል ስራኣስከያጅ የሆኑት ኣቶ ዕርድያ ኣሰፋ በበኩላቸው በዚህ ኣመት ብቻ በወረዳው በደስታ ወይንም ኣባ ሰንጋ በሽታ 99 ሰዎች መጠቋታቸውና 4 መሞታቸውም ይገልፃሉ ፡፡

በተለምዶ የደስታ ወይም ኣባሰንጋ የተባለ የእንስሳት በሽታ መስፋቱ ተከትሎ እንስሳቱ ለሞት እየተጋለጡ በመሆኑ   የወረዳዋ ነዋሪዎች ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውም  ይናገራሉ፡፡

በአበርገለ የጭላ ወረዳ የእንስሳት ሃኪም የሆኑት ኣቶ ብርሃነ ልኡል እንደገለፁት  ለበሽታው መከሰት ዋና መንስዔ እንስሳቱ ክትባት ኣለማግኘታቸው ተከትሎ መሆኑና ፋሽስቱ የአብይ ቡድንና ግብረአበረቹ ምንም ኣይነት መድሃኒት እንዳይገባ መከልከሉ ተከትሎ በዚህ 3 ዓመት ምንም ዓይነት ክትባት ኣላገኙም ብለዋል፡፡

በዚህም የተነሳ ይላሉ ኣቶ ብርሃነ በወረዳው ብቻ ከ7 ሺ በላይ እንስሳት መሞታቸውንም ያብራራሉ፡፡

ይህንን የእንስሳቱ በሽታ ቀስ በቀስ ወደ ሁሉም የአገሪቱ አከባቢዎች ከመዛመቱ በፊት የሚመለከታቸው አካላት የፋሽስቱ ቡድን ያነረው ከበባና ክልከላ እንዲያበቃ መስራት ይገባቸዋል ሲሉም ነዋሪዎቹና የእንስሳት ሕክምና ባለሞያዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

መዓዛ መኮነን

Previous articleበአምባገነኑ የኢሳያስ ቅጥረኛ ወታደሮች በዋግ ህምራ ጤና ጣብያን በማውደማቸው ነዋሪዎች የህክምና አገልግሎት መቸገራቸው ገለፁ።
Next articleከአፍሪካ መሪዎች ጋር በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ ፋሽስቱ አብይ  እንዳይሳተፍ የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤትና የህግ መወሰኛ ም/ቤት   ስምምነት ላይ  ደረሱ፡፡