Home ዜና በትግራይ አለም ትኩረት ያልሰጠው ጀኖሳይድ እየተፈጸመ ነው ተባለ

በትግራይ አለም ትኩረት ያልሰጠው ጀኖሳይድ እየተፈጸመ ነው ተባለ

1116
0

በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ተወልዳ ያደገችው የአርተፊሻል ኢንተልጀንስ ተመራማሪ ትምኒት ገብረ በትግራይ አለም ትኩረት ያልሰጠችው ጀኖሳይድ እየተፈጸመ ነው ብላለች፡፡

በጀኖሳይድ ወንጀሉ ግማሽ ሚሊዮን የትግራይ ህዝብ ህይወት ሊቀጠፍ ችሏል የምትለው ትምኒት ገብሩ፤ አሁንም የትግራይ ህዝብ ምግብና መድሃኒትን ጨምሮ ሁሉም መሰረታዊ አገልግሎቶችን ተከልክሎ ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቁን ትናገራለች፡፡

በትግራይ ተጠልለው የነበሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ስደተኞች ደብዛቸው መጥፋቱን ነው የምትናገረው ትምኒት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ጀኖሳይድን ያስከተለ ጦርነት እየተካሄደ ነው፡፡

የጀኖሳይድ ወንጀሉም በትግራይ ላይ ነው እየተፈጸመ ያለው፡፡ ባለፉት አስራ ስምንት ወራት ግማሽ ሚሊዮን የሚገመት የትግራይ ህዝብ ህይወቱ ሊቀጠፍ ችሏል፡፡ ሰባት ሚሊዮን የትግራይን ህዝብ ደግሞ ላለፉት አስራ ስምንት ወራት ምንም አይነት ምግብ፣ መድሃኒት እና ኢንተርኔት እንዳያገኝ ተከልክሏል፡፡ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የኤርትራ ስደተኞችም ያሉበት አይታወቅም፡፡

በአሁኑ ጊዜ በአለማችን ደም አፋሳሹ ጦርነት በዩክሬን ሳይሆን በትግራይ መሆኑን የምትገልጸው ትምኒት፤ በትግራይና በዩክሬን ጦርነት የሞቱትን ዜጎች ለንጽጽር የሚቀርብ አይደለም ስትልም አስተያየትዋን ሰጥታለች፡፡

The Washington post እንደጻፈው የአለማችን ደም አፋሳሹ ጦርነት በዩክሬን ሳይሆን በትግራይ ነው ያለው፤ በትግራይ ያለውን ሁኔታ እና በሌሎች ግጭት ባለባቸው አገራት ብናነጻጽር እንኳን በዩክሬን ጦርነት ወደ ሶስት ሺህ የሚጠጉ ንጹሃን ዜጎች መሞታቸውን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ጽህፈት ቤት ይፋ ተደርጓል፡፡ በአንጻሩ በትግራይ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህዝብ መሞቱን Gent ዩኒቨርስቲ ይፋ አድርጓል፡፡

ትምኒት ገብሩ ከሌሎች የአርተፍሻል ኢንተልጀንስ ተማራማሪዎች ጋር በመሆን Google በሴቶች ላይ የሚፈጽመው አድላዊ አሰራርና የቆዳ ቀለምን መሰረት ተደርጎ የሚፈጸሙ አግላይ አሰራሮችን በማጋለጥ በርካታ አድናቆት ያተረፈች ሰትሆን፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2021 በፎርችን ከ50ዎቹ የአለማችን ምርጥ መሪዎች መካከል አንዷ ተብላ የተሸለመች ናት፡፡

ባለፈው ሳምንት ደግሞ ታይም መጽሄት ከአንድ መቶዎቹ የአለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ውስጥ  ተካታለች፡፡

Previous articleየዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳሬክተር በትግራይ ላይ የጤና ስርዓቱ አገልግሎት መስጠት ወደ የማይችልበት  ቁመና  መድረሱን አስታወቁ፡፡
Next articleበኦሮሚያ ነፃነት ጦርና በተስፋፊው የአማራ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን ተዘገበ፡፡