Home ዜና በትግራይ የሚገኙ የትምህርት ተቋማት መውደማቸውን ተከትሎ በተማሪዎች ስነ ልቦና ላይ ከፍተኛ ጫና...

በትግራይ የሚገኙ የትምህርት ተቋማት መውደማቸውን ተከትሎ በተማሪዎች ስነ ልቦና ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩ ተነገረ፡፡

620
0

በፋሽስቱ የአብይ ቡድን እና ግብረ አበሮቹ በትግራይ ህዝብ ላይ በታወጀውን የጆኖሳይድ ጦርነት በትግራይ የሚገኙ በርካታ የትምህርት ተቋማት መውደማቸውን ተከትሎ ለመማር ማስተማር እና በተማሪዎች ስነ ልቦና ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩን ተገለፀ፡፡

የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ምኞች ያልተሳካላቸው የፋሽስቱ የአብይ ቡድን እና ግብረ አበሮቹ በትግራይ የተማረና ጠያቂ ትውልድ እንዳይፈጠርና እንዲደነቁር ከትምህርት ገበታ እንዲርቅ አላማ አንግበው የትግራይ ትምህርት ቤቶች ሆን ተብሎ እንዲወድሙ መደረጉን የመቐለ ዩኒቨርስቲ የስርአተ ትምህርት ባለሙያ ዶክተር ታደሰ ካህሳይ ገልጸዋል፡፡

በተለይ ደግሞ ፋሽስቱ የአብይ ቡድን እና ግብረ አበሮቹ በትግራይ ህዝብ ላይ ያኖሩትን ከበባ እና ክልከላ ተከትሎ በአሁኑ ጊዜ የትግራይ ተማሪዎች ከትምህርት መራቃቸውን የገለጹት ዶክተር ታደሰ ከቅደመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ የሚማሩ ህጻናትና ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ በመራቃቸው በመማር ማስተማር ላይ የሚፈጥረው ጫና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

የፋሽስቱ ቡድን ትውልድን የሚያንጹ የትምህርት ተቋማት የማውደምና የመዝረፍ ተግባር ሲፈፅሙ በድንገት ሳይሆን ሆነ ተብሎ እንደሆነ በመግለጽ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሚማሩ ተማሪዎችም ከባድ ጫና አሳድረዋል ብለዋል፡፡እንደ ዶክተር ታደሰ ገለጻ በቀጣይ ለትግራይ እድገትና ልማት የተለየ አቅም ያለው በቴክኖሎጂ የሰለጠነ የሰው ሀይል የሚያፈሩ የነበሩትን ኮሌጆች እና የቴክኒክ ሙያ ተቋማት በፋሽስቱ ቡድን ወድመዋል ፡፡

ይህ ሁሉ በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያልው የጆኖሳይድ ወንጀል በተለይ በትምህርት ቤቶች ትኩረት ማድረጋቸው በትግራይ ከእውቀት ነጻ የሆነ የተማረ የሰው ሀይል እንዳይኖር ካላቸው ፍላጎት የተነሳ ነው የሚሉት ዶክተር ታደሰ ይህ የፋሽስቶች ሴራ እና እኩይ ተግባር ተማሪዎች ወላጆች እና መንግስት በአንድነት ተቀናጅተው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል ፡፡

መአዲ ሃይለ

Previous articleአለም አቀፍ የተጋሩ ባለሙያዎችና ምሁራን የአቋም መግለጫ
Next article“የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች”