Home ዜና በትግራይ የጀኖሳይድ ጦርነት የክልሉን በጤና ስርዓት ውድመት

በትግራይ የጀኖሳይድ ጦርነት የክልሉን በጤና ስርዓት ውድመት

805
0

የትግራይ ጤና ስርዓት ሙሉ በሙሉ እንዲውድም በመደረጉ የጤና ባለሞያዎች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በሽተኞችን የህክምና አገልግሎት ለመስጠት እንደተቸገሩ የጤና ባለሞያዎች ገለፁ፡፡

New humanitarian ፋሽስት አብይና ተባባሪዎቹ በትግራይ ህዝብ ላይ ባካሄዱት የጀኖሳይድ ጦርነት የክልሉን ጤና ስርዓት ሙሉ በሙሉ እንዲወድም በማድረግ የትግራይ ህዝብ ለከፋ የህክምና ችግር እንደዳረጉት አስነብቧል

በደረሰው ውድመትም የመድሃኒትና የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶች እጥረት በጣም አስከፊ በመሆኑ የተነሳ በጠና ለታመሙ በሽተኞች የመጠቀሚያ  ጊዜ ያለፈባቸው መድሀኒቶች ለመስጠት መገደዳቸውን በዘገባው አመላክቷል፡፡

በተለይም ከኤች አይቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ሰዎችን ጨምሮ በካንሰርና በስኳር  በሽታ ለሚሳቃዩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ህመምተኞች ለወራት ያህል ስቃይ ውስጥ ናቸው ብለዋል፡፡

የቀዶ ህክምና ለማድረግ አሮጌ ጨርቅ ከማህበረ-ሰቡ እንደሚቀበሉና አገልግሎት ላይ የዋሉ  የናሙና መውሰጃ ከረጢት፣ የቀዶ ህክምና መገልገያ ግላብ መልሰው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ እየተደረገ መሆኑና ለእጥበት አገልግሎት የሚያገለግለው   ዲተርጀንት የተባለ ኬሚካል ደግሞ አለመኖሩን New humanitarian በዘገባው አመላክቷል፡፡

በዓይደር ሆስፒታል የሚሰራ  ሃኪም በመጥቀስ New humanitarian እንደዘገበው መሰረታዊ የሚባሉ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች፣  መድሀኒቶችና መለዋወጫ እቃዎች በመዘረፋቸው የጤና ስርዓቱ በበርካታ ቀዳዳዎች የተፈተነ ነው ብለዋል፡፡

በጤና ስርዓቱ ላይ ተከስቶ ያለውን ሁኔታ 16ኛና17ኛ ክፍለዘመን የሚያመላክት እንጂ የ21ኛ ክ/ዘመን መሆኑ የሚያሳይ ነገር የለውም፡፡ ምክንያቱም በሽተኞች በመድሂነት እጦት ምክንያት ፊት ለፊትህ ይሞታሉ ሲሉም ነው የጤና ባለሞያዎቹ የተናገሩት፡፡

በትግራይ በጤና ስርዓቱ ላይ ሆን ተብሎ በተፈጠረው ውድመት ቁስል ያለባቸው ሰዎች ጨው የተቀላቀለበት የሞቀ ውሃ ለማጠብ መገደዳቸውና በነዳጅ እጦት ምክንያት ነብሰ-ርጡር እናቶች በእግራቸው እንዲጓዙ አልያም በሰው ትከሻ እንዲጓዙ መገደዳቸውና ጤና ተቋማት በከፍትኛ  የሃይል መቆራረጥ እየተፈተኑ መሆናቸውን ዘገባው አመላክተዋል፡፡

የዓይደር ሆስፒታል ለበሽተኞች ሲያቀርበው የነበረ  የምግብ አገልግሎት በማቋረጡ  በሆስፒታሉ ውስጥ የህክምና ክትትል ሲደረግባቸው የነበሩ 240   በሽተኞች ምግብ ገዝተው ለመመገብ ባለመቻላቸው ምክንያት ወደ ቤታቸው መሸኘታቸውን በዘገባው አስታውሶአል፡፡

አዳዲስ በሽተኞችም ምግብም ይሆን ገንዘብ ስሌላቸው በሆስፒታሉ ለቀናት ያህል ቆይተው የህክምና አገልግሎት ለማግኘት እንደማይችሉ ዘገባው አመላክተዋል፡፡

በትግራይ የህክምና አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ በርከታ ዶክተሮች አሁን ለህዝባቸው የህክምና አገልግሎት እየሰጡ አይደለም ያለው የ New humanitarian ዘገባ  ምክንያቱ ደግሞ ጦርነቱ ባስከተለው መፈናቀል ሰለባ ሆነዋል አልያም ምግብ ፍለጋ  ላይ ናቸው  ብለዋል፡፡

የጤና ስርአቱ ሙሉ በሙሉ እንዲወድም ቢደረግም እኛ ባለን አቅም ለህዝባቸን  ለማገልገል የቻልነውን ሁሉ ከማድረግ አንቆጠብም፡፡ ነገር ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ነገሮች ከባድ እንደሆኑ በዓይደር ሆስፒታል አንድ ዶክተር በመጥቀስ ዘገባው አመላክተዋል፡፡

በፋሽስት አብይ ቡድን ግብዣ ትግራይን የወረረው የአምባገነኑ ኢሳያስ ወታደሮች  የጤና መሰረተ ልማቶች ሆን ብለው እንዲውድሙና የቻሉትን ያህል ደግሞ ወደ ኤርትራ ጭነው እንደተጓዙ ዘገባው አመላክቷል፡፡

በትግራይ በጤና ዘርፉ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት 40 ሆስፒታሎችን ጨምሮ 90 በመቶ የሚሆኑ ጤና ተቋማት መውደማቸውና የኤርትራ ወታደሮች መሰረታዊ የሚባሉ የህክምና መሳሪያዎች በተሽከርካሪዎችና በሄሌኮፕተር ጭምር ሲያጓጉዙት መመልከቱን መዲክስ የተባለ ድህረ ገፅ መዘገቡን አውሱቷል፡፡

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በሽተኞች የት እንዳሉ መረጃው እንደሌለ የጠቀሰው ዘገባው ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት 46ሺህ የስኳር ህመምተኞች ክትትል ይደረግባቸው እንደነበረና አሁን ከቀይ መስቀል የተገኘው የስኳር መድሀኒት ለጥቂት ሰዎች ብቻ የሚያገለግል መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በመብራህቱ ይባልህ 

Previous articleከፋሽስቱ የአብይ ሰራዊት ጋር ውጊያ ውስጥ የገባው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ ድል ማስመዝገቡን  አስታወቀ።
Next articleበጎንደር ከተማ በፅንፈኛው ፋኖ የተገደሉት የሙስሊም ማህበረ-ሰብ አባላት በተለያዩ የማህበረ-ሰብ ክፍሎች ዘንድ ቁጣን ቀሰቀሰ።