Home ዜና በትግራይ የጄኖሳይድ ጦርነት ምክንያት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እጅግ ማሽቆልቆሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

በትግራይ የጄኖሳይድ ጦርነት ምክንያት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እጅግ ማሽቆልቆሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

549
0

በትግራይ የጄኖሳይድ ጦርነት ምክንያት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እጅግ ማሽቆልቆሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ያወጣው የአገሪቷ የ2022 የኢንቨስትመንት ሁኔታን የገመገመ መረጃ ጠቆመ፡፡

የአሜሪካ ኤምባሲ ባወጣው በዚሁ የኢትዮጵያ የ2022 የኢንቨስትመንት ደረጃን አስመለክቶ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2021 በርካታ የኢኮኖሚ ተግዳሮቶች እንደ አጋጠሙዋት ጠቅሶ ለተፈጠረው የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል ምክንቶች የትግራይ የጀኖሳይድ ጦርነት፣ በመላ አገሪቱ የተከሰቱ የፖለቲካ ቀውሶች፣ በደቡባዊና ምስራቃዊ ቆላማ አገሪቱ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ እንዲሁም ከኮቪድ 19 ጋር የተያያዙ ችግሮች መሆናቸውን አብራርቷል፡፡

አጠቃላይ አገሪቷ ማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ መገለጫው ከ30 በመቶ በሚበልጥ ዋጋ ግሽበትናውሱን ውጭ ምንዛሪ ክምችት የሚንቀሳቀስ መሆኑን  የገለጸው አሜሪካ ኤምባሲ መግለጫ  ከፍተኛ የበጀት ጉድለትና የዕዳን የመክፈል አቅምን መመናመን መለያ ባህሪውን መሆኑን አስረድቷል፡፡

በአለምአቀፉ ገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ ትንቢት መሰረት አገሪቷ ኢኮኖሚ በ2020 ከነበረበት 6 በመቶ ኢኮኖሚ እድግት በ2021 ወድ 2 በመቶ መውረዱና ከዛ በፊት ለአመታት የታው የባለሁለት አሃዝ ኢኮኖሚ እድገት ጋር ሲነጻጸር  ኢኮኖሚው በእጅጉ ማሽቆልቆሉን ይሄው የአሜሪካ ኤምባሲ መግለጫ ያትታል፡፡

በኢትዮጵያ ቢዝነስ ለማካሄድ  የሎጂስቲክ የሙስናና የቢሮክራሲ ማነቆዎች እንዲሁም በትራንስፖርት መወደድ አስቸጋሪ እንዳደረገው ያብራራው መግለጫው  በአሳሳቢ ሁኔታ የሚገኘው ውጭ ምንዛሪ እጥረት የውጭ ኩባንያዎች የሚያገኙትን ትርፍ ወደ አገራቸው ለመላክ  እንዳይችሉ እንዲሁም ብር  ከሌላ ገንዘብ ጋር በቀላሉ ሊመነዘር የማይችል በመሆኑ  በዚሁም የኢንቨስትመንት ግብአት እንዳያገኙ እንዳደረጋቸው ጠቁሟል፡፡

ወደ ውጭ የሚላከውን ምርት አፈፃፀም  አሁንም ደካማ መሆኑን  ያመለክታል መግለጫው፡፡

በትግራይ ህዝብ ላይ የታወጀው የጀኖሳይድ ጦርነት፣ እንዲሁም  በአገሪቱ የሚታውን የፖለቲካ አለመረጋጋትና የጸጥታ ቀውስ የአገሪቷን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እንዳይስብ ምክንያት እንደሆነ መግለጫው አክሏል፡፡

በኩኖም ቀለሙ

Previous articleበሳውዲ ዓረቢያ የእስር ጊዝያቸውን ያጠናቀቁ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሃገራቸው መምጣት ቢፈልጉም ፋሽስቱ የአብይ ቡድን አልቀበላችሁም በማለቱ መምጣት እንዳልቻሉ BBC ዘገበ፡፡
Next articleየትግራይ መንግስት ከአውሮፓ ህብረትና  ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኞች፤ የአውሮፓ አገራት አምባሳደሮች በሰላማዊ ድርድሩና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡