Home ኣማርኛ ዜና በአሜርካ ኦሪገን የተጋሩ አትሌቶች ድል የትግራይ ዲያስፖራ ማህበረ-ሰብ ለህዝባቸው ድምፅ ለመሆን እድሉን...

በአሜርካ ኦሪገን የተጋሩ አትሌቶች ድል የትግራይ ዲያስፖራ ማህበረ-ሰብ ለህዝባቸው ድምፅ ለመሆን እድሉን እንደተጠቀሙበት ተገለፀ፡፡

848
0

በአሜርካ ኦሪገን በመካሄድ ያለው 18ኛው የአለም የአትለቲክስ ሻምፒዮን ለይ ጀግኖች የትግራይ ዲያስፖራ ማህበረሰብ ለትግራይ ህዝብ ድምፅ ለመሆን እድሉን እንደተጠቀሙበት ተገለፀ፡፡

በተለያዩ  የአለማችን  ክፍሎች የሚገኙ የትግራይ ዳያስፖራ ማህበረሰብ  ባገኙት አጋጣሚ  ለትግራይ ህዝብ ድምፅ በመሆን ፋሽስቱ የአብይ ቡዱንና ሸሪኮቹ በትግራይ ህዝብ ላይ  የፈፀሙት እና እየፈፀሙት  ያለውን የጆኖሳይድ ወንጀል ተዳፍኖ እንዳይቀር የአለማቀፍ ማህበረሰብ እንዲያውቀው  እና የሚመለከታቸው አካላት  በአፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰዱበት ድምፃቸውን እያሰሙ ይገኛሉ ፡፡   

በትግራይ ህዝብ ላይ እልቂት የፈረዱ የፋሽስቱ አብይ ቡድንና ግብረአበረቹ  የትግራይ ተወላጆች  ሲያሸንፉ የሚደሰቱ ስለ ትግራይ ችግር ግን ማፈን የሚቀናቸው መሆናቸውን አሁንም በድጋሜ በዓለም መድረክ አሳይተዋል፡፡

በአሜሪካ ኦሪጎን በአምስት ሺህ ሜትር ወርቅ ላጠለቀችው አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ  የውጭ መገናኛ ቡዝሃን  ስለ ትግራይ ሰንደቅ አላማና ስለ ትግራይ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ያቀረቡላትን ጥያቄ በቦታው በአስተርጋሚነት የቀረበው የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተወካይ የአትሌትዋን ድምፅ በአደባባይ ሲያፍን ተስተውሏል፡፡

የትግራይ ተወላጅ አትሌቶች በኦሪጎን ከተማ በድል ቢያሸበርቁም በቤተሰቦቻቸውና በትግራይ ህዝብ እየደረሰ ያለውን የጀኖሳይድ ጦርነት ግን ለአለም ማስተጋባት አልቻሉም፡፡ በአትሌቶቹ እና  በትግራይ ህዝብ  ፋንታ   ድምጽ ልሁን ያለው በአሜሪካ የሚኖር የትግራይ ተወላጅ ዳያስፖራ ማአርግ መኮነን የአለም ሚድያዎችን ቀልብ ስቦ ውሏል፡፡ ስሜቱን  መቋቋም ያቃተው ማእርግ ወደ መሮጫ ሜዳ በመግባትም ከአትሌቶች ጋር ደስታውን ገልጿል፡፡ 

ለትግራይ ህዝብ አጋርነቱ በገለፀለት ግዜ አግራሞትን የፈጠረባቸው ማአርግ የውጭ አገር ጋዜጠኞች ላቀረቡለት ጥያቄም ላለፉት አመታት የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያን የገነባ መሆኑን ተዘንግቶ በፋሽስቱ ቡድንና ሸሪኮቹ በላዩ ላይ የጆኖሳይድ ወንጀል እየተፈፀመበት ይገኛል ብሏል፡፡

በአሜሪካ ኦሪገን በተካሄደው የአለም አትለቲክስ ሻምፒዮና የትግራይ ተወላጅ አትሌቶች ሰሶት  የወርቅ ሜዳልያ   ማስገኘታቸው  ተከትሎ   በአለማችን የሚገኙ  ተወቂ ሰዎች  እና የፖለቲካ ተንታኞች አስታያየታቸው እየሰጡበት ይገኛሉ ፡፡

መአዲ ሀይለ

Previous articleበትግራይ የእርሻ መሳርያዎች እና ግብአቶች በአፋጣኝ ለአርሶአደሩ እንዲዳረስ አራት የአለምአቀፍ ዩንቨርስቲዎች ተመራማሪዎች እና ምሁራን ጠየቁ፡፡
Next articleበኢትዮፕያ ያጋጠመው የኢኮኖሚ ቀውስና  የእዳ መቆለል በፋሽስቱ ቡድን   ለወታደራዊ አገልግሎት በማዋሉ መሆኑየዓለም ባንክ ገለፀ፡፡