Home ዜና በአገው ቢርቢጣ ወረዳ በሰው ሰራሽ ረሃብ ምክንያት የ14 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተገለፀ።

በአገው ቢርቢጣ ወረዳ በሰው ሰራሽ ረሃብ ምክንያት የ14 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተገለፀ።

821
0

ፋሽስት የአብይ ቡድን እና ተስፋፊው የአማራ ሃይል ረሃብ እንደ ጦር መሳርያ በመጠቀም ጆኖሳይድ መፈጸም አዲስ ባይሆንባቸውም አሁንም የአገው ህዝብ አንበርክኮ ለመግዛትና ለመጨፍለቅ ሁለንተናዊ ከበባው አጠናክረው እየቀጠሉበት ይገኛሉ።

በዚህም የቅዳሚት፣ ጻግቭጂ፣ አበርገሌና ከፊል ሰቆጣ ዙርያ ከተስፋፊው የአማራ ሃይል ነጻ የወጡ በአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሰራዊት ስር ባሉ ቀበሌዎች እርዳታ እንዳያገኙ ከተከለከሉ የአገው ወረዳዎች ተጠቃሽ ናቸው።

ከነዚህም በቢርቢጣ ንኡስ ወረዳ የአምስት ቀበሌዎች ተወካዮች ከእርዳታ ድርጅቶች  ህዝቡ ምንም ዓይነት እርዳታ እንዳላገኘና እርዳታውም ለታለመለት አላማ እየዋለ እንዳልሆነ እንዲሁም ህዝቡ ለሞትና ለተለያዩ በሽታዎች ተጋልጦ እንደሚገኝ ይናገራሉ፡፡

ተወካዮቹ ጨምረው እንዳሉት የአለም አቀፍ የሰብአዊ እርዳታው በሴፍትኔትም ሆነ በአስቸኳይ እርዳታ ሰቆጣ ላይ እየገባ ቢሆንም በቢርቢጣ ንኡስ ወረዳ ግን ላለፉት 14 ወራት ምንም አይነት እርዳታ እንዳልገባላቸው ተናግረው ሰቆጣ ገባ የተባለው እርዳታም ተስፋፊው የአማራ ሃይሎች በአጭበርባሪዎች እያስፈረሙ እየዘረፉት መሆናቸው አጋልጠዋል።

የቢርቢጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አለፈ ብርሃኑም በተደጋጋሚ ለአለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶችና ለሚመለከታቸው አካላት እንዳሳወቁ ገልጸው በተደረገው ክልከላ ምክንያት ህዝቡ ለከፋ የረሃብ አደጋ እንደተጋለጠ እና በንኡስ ወረዳው በረሃብ ምክንያት የ14 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተናግረዋል።

የአለም አቀፍ መንግስታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ከጠላት ነጻ በሆኑ ከዚህ በፊት በነበሩት የእርዳታ መከፋፈያ ጣብያዎች በኩልም ለህዝቡ አስቸኳይ የሰብአዊ እረዳታ እንዲያቀረቡለት አስተዳዳሪው ጥሪ አቅርቧል።

የህዝቡን ህይወት ለመታደግ ዓለም አቀፋ የእርዳታ ድርጅቶች ለነዚህ አከባቢዎች እርዳታ እንዳይደርስ በአምባገነኑ ቡድንና በተስፋፊዎቹ ሆን ብለው በመከልካላቸውና የውሸት ፕሮፓጋዳዎች በመንዛትና ክልከላው በማጠናከር አሁንም ህዝቡ ለከፍተኛ የረሃብ አደጋ ተዳርገዋል፡፡ ይህንን ሰው ሰራሽ የረሃብ አዳጋም እንዲቀለበስ የሚመለከታቸው አካላት ሊደርስሏቸው እንደሚገባ ተገልፀዋል፡፡

ሓጋዚ ኣብርሃ

Previous articleየትግራይ ሴንተራል ኮማንድ አባል አቶ ጌታዉ ረዳ  ሶስተኛዉ ዙር  የዲያስፖራ የመመከት ዘመቻ በድል እንዲጠናቀቅ   ጥሪ አቀረቡ፡፡
Next articleየትግራይ መንግስት መግለጫ