Home ዜና በኦሉሴጉን ኦባሳንጆ የቀረበው የአምባገነኑ ኢሳያስ ወደ ሰላም ድርድሩ መጋበዝ የሰላም ድርድሩ ለማደናቀፍ...

በኦሉሴጉን ኦባሳንጆ የቀረበው የአምባገነኑ ኢሳያስ ወደ ሰላም ድርድሩ መጋበዝ የሰላም ድርድሩ ለማደናቀፍ መሆኑ ተነገረ፡፡

1116
0

—-

በፋሽስቱ የአብይ ቡድንና በትግራይ መንግስት መካከል ይካሄዳል ተብሎ በሚታሰበው የሰላም ድርድር  የአምባገነኑ ኢሳያስ ወደ ሰላም ድርድሩ መጋበዝ የሰላም ድርድሩ ለማደናቀፍ  በሌላ በኩል ደግሞ አምባገነኑ ኢሳያስ በትግራይ ህዝብ ላይ የፈፀመዉ ጀኖሳይድ ከተጠያቂነት ለማምለጥና ከለላ ለመስጠት ያለመ መሆኑ ተገለፀ፡፡

በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የፖለቲካ አለመረጋጋት አስመልክተው ለአፍሪካ ህብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት  በትግራይ መንግስትና በፋሽስት የአብይ ቡድን መካከል ሊደረግ በታሰበው የሰላም ድርድር ላይ አምባገነኑ የኢሳያስ መንግስት ተሳታፊ እንዲሆን መጋበዛቸዉ ፍታሃዊነት የጎደለዉና የሰላም ድርድሩ ለማደናቀፍ የሚችል ነዉ ይላሉ የፖለቲካል ሳይንስ ሙሁርና የፖለቲካል ተንታኞች፡፡

ልዩ መልእክተኛው ኦባሳንጆ የአምባገነኑ ኢሳያስ አሁንም ከሉኣላዊ የትግራይ ግዛት ሳይወጣና በትግራይ የጀኖሳይድ ጦርነት ከእቅድ እስከ አፈፃፀም ድረስ መላ አቅሙን በማስተባበር መሳተፉ እየታወቅ በፋሽስቱ የአብይ ቡድንና በትግራይ መንግስት መካከል ይካሄዳል ተብሎ በሚታሰበው የሰላም ድርድር አምባገነኑ ኢሳያስ ይሳተፍ ማለት አገሪቷ እንደትፈርስ ማድረግ፣ የአገሪቷን ሉአላዊነት አሳልፎ የመስጠትና ኤርትራ የኢትዮዽያ አካል ሁናለች ማለት ነዉም ብለዋል  የፖለቲካል ተንታኞቹ፡፡

የፖለቲካል ሳይንስ ሙሁሩ አክለውም የትግራይ ህዝብን በከበባና በክልከላ እንዲሰቃይ እያደረገ ባለበት ወቅት ለሰላም ድርድሩ ዝግጁ ነኝ ማለቱ ፋሽስቱ የአብይ ቡድን የሰላም ድርድሩ ለጀኖሳይድ  እየተጠቀመበት እንደሆነም ገልፀዋል፡፡ 

ሰላም ለመፍጠር የሁለቱ አካላት መልካም ፍላጎት ያስፈልጋል ያለዉ ምሁሩ የትግራይ መንግሰት በተደጋጋሚ ለሰላም ቅሩብ መሆኑ በተደጋጋሚ እየገለፀ የመጣና ነገር ግን ፋሽስት ቡድኑ በእጁ ያለዉ መፈፀም ያልቻለና የሰላም ተነሳሽነት የሌለዉ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

ፍረወይኒ መንገሻ 

Previous articleተስፋፊው የአማራ ሃይል በሃይማኖት ሽፋን ፖለቲካን የሚያራምዱ ሃይሎች መድቦ ታሪክና ቅርስ እየዘረፈ መቆየቱን ተገለፀ፡፡
Next articleየትግራይ ህዝብ ያጋጠመው ችግር ለመፍታትና ዋስትናዋን የተረጋገጠ ትግራይን ለመገንባት የታጋይ መለስ ዜናዊ ራኢ ማስቀጠል  ይገባል ተባለ