Home ዜና በዓለማችን በሚገኙ 20 ሃገራት ውስጥ እጅግ የከፋ ረሃብ ሊከሰትባቸው እንደሚችል የዓለም OCHA...

በዓለማችን በሚገኙ 20 ሃገራት ውስጥ እጅግ የከፋ ረሃብ ሊከሰትባቸው እንደሚችል የዓለም OCHA እና WFP አስጠነቀቁ፡፡

788
0

የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት እና የዓለም የምግብ ፕሮግራም በዓለማችን በሚገኙ 20 ሃገራት ውስጥ አሁን ያለውን የምግብ አቅርቦት እጥረት ከወዲሁ ካልተፈታ እጅግ የከፋ ረሃብ ሊከሰትባቸው እንደሚችል አስጠነቀቁ፡፡

ሁለቱም ድርጅቶች ከፍተኛ የረሀብ አደጋ በሚታይባቸው እና በመጀመሪያ ረድፍ ከሚገኙ 20 ሃገራት መካከል ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በብልጽግና ጎዳና ላይ እየገሰገሰች ነች የሚላት ኢትዮጵያን ተጠቃሽ መሆኗዋን ሪሊፍ ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡

የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት /ፋኦ/ እና የዓለም ምግብ ፕሮግራም /WFP/ በጋራ በዓለማችን የፖለቲካ ትኩሳት በሚታይባቸው 20 ሃገራት ያለው የሰብአዊ ቀውስ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሪፖርትን ጠቅሶ ሪሊፍ ድረ ገጽ እንደዘገበው፣ በሃገራቱ የሰብአዊ ድጋፍ ከወዲሁ ካልተደረገ ከፊታችን ሰኔ ወር እስከ መስከረም 2022 ድረስ እጅግ የከፋ የምግብ እጥረት ሊያጋጥም ይችላል ብለዋል፡፡

እንደ የአውሮፓ ዘመን አቆጠጣር ባለፈው ግንቦት 2022 ይፋ በተደረገው የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሪፖርት፣ የፋሽስቱ የአብይ ቡድን በብልፅግና ጎዳና ላይ ወደ ፊት እየገሰገሰች ነች የሚላት ኢትዮጵያን ጨምሮ ናይጀሪያ፣ ደቡብ ሱዳን እና የመን በምግብ እጥረት የሚሰቃዩና በቀጣይም ኩፍኛ የምግብ አቅርቦት ችግር ምክንያት ከፍተኛ የማስጠንቀቂያ ደወል ከሚያቃጭልባቸው ሃገራት ረድፍ የሚቀድማቸው የለም ብለዋል፡፡

አፍጋኒስታንና ሶማሊያ ደግሞ በሰብአዊ ቀውሱ ውስጥ ከተቀላቀሉ አዳዲስ ሃገራት መካከል ይጠቀሳሉ ያለው ድረ ገጹ፣ የተጠቀሱት ሃገራት በረሃብ ደረጃ አመላካች መስፈርት የመጨረሻ የሆነው አምስተኛ ደረጃ መያዛቸውን አመልክቷል፡፡

ኢትዮጵያ፣ የመን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያና አፍጋንስታን ውስጥ እስከ አሁን ድረስ ከ 750 ሺህ በላይ ሰዎች በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ እና ከፊሎችም በረሃቡ ምክንያት ለሞት መዳረጋቸውን በዘገባው አስታውሷል፡፡

በዩክሬን የታወጀው ጦርነት በሃገራቱ ውስጥ የነበረውን የረሃብ አደጋ እንዲቀጥል አድርጓል፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የረሃብ ማእበል እንዲስፋፋና ዓለም የተከሰተውን የረሃብ ቀውስ ለመቋቋም የሚያስችል የምግብ አቅርቦት አቅም እንዳሳጣት ዘገባው አመልክቷል፡፡

ኮንጎ፣ ሃይቲ፣ ሶሪያ የሳህል ቀጠና፣ ሱዳን መሰል ሃገራት ደግሞ የረሃብ አደጋው ተጋላጭ ናቸው ያለው ሪሊፍ ድረ ገጽ፣ ኬንያም ወደ ችግሩ አዲስ ገቢ መሆኗዋን ገልጿል፡፡ 

አሁን ባለው ግጭት ምክንያት የተከሰተወ የረሃብ ቀውስ ከሰኔ እስከ መስከረም ወራት ድረስ  ሊከሰቱ ከሚችሉ የጎርፍ፣ የአየር ለውጥ፣ ሄሪኬይን፣ የሰዎች መፈናቀልና ከሌሎች ችግሮች ጋር ተዳምሮ የረሃብ ቀውሱ እጅግ ከፍ ሊያደርገው እንደሚችልም ሚሊዮን ህዝቦችን ለረሃብ አደጋ እንደሚዳርግ ነው ሪሊፍ የዘገበው፡፡

ዩክሬንን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የዓለም ሃገራትም በቀውሱ ትኩሳት ውስጥ በቅርቡም ሊካተቱ እንደሚችሉ ዘገባው አመልክቷል፡፡

አማረ ኢታይ  

Previous articleፋሽስት አብይ አሕመድ በትግራይ ህዝብ ላይ ፍፁም ረሃብ የሚባል ነገር የለም በማለት መካዱን የዓለም ሰላም ድርጅት አጋለጠ፡፡
Next articleየትግራይ ምሁራንና ባለሙያዎች ማህበር ከትግራይ ህዝብ ጎን በመቆም ታሪክ የማይረሳው ድልመስራቱ የትግራይ መንግስት ገለፀ፡፡