Home ዜና በዓላማችን በማደግ ባሉ ሃገሮች የምግብ እጥረት የብዙሃን ረሃብና የረሃብ ቸነፈር ሊያመራ እንደሚችል...

በዓላማችን በማደግ ባሉ ሃገሮች የምግብ እጥረት የብዙሃን ረሃብና የረሃብ ቸነፈር ሊያመራ እንደሚችል WFP ሪፖርት  አስታውቋል።

671
0

——

ከየካቲት ወር ጀምሮ እየቀጠለ ባለው የሩስያና ዩክሬን ጦርነት ሳቢያ በዓላማችን በማደግ ባሉ ሃገሮች ከፍተኛ የምግብ እጥረት ማጋጠሙን ያመለከተው በምግብ ቀውስ ላይ ያተኮረ የ2022 ግሎባል ሪፖርት ቀውሱ ለከፍተኛ የተመጣጠነ የምግብ እጥረት የብዙሃን ረሃብና የረሃብ ቸነፈር ሊያመራ እንደሚችል አስታውቋል።

በዚሁ ቀውስ 40 ዓመት ሃገራት ውስጥ 180 ሚሊዮን ህዝብ ሊጋፈጡ በሚያችሉ የምግብ ዋስትና እጥረት ይኖራሉ የሚለው ሪፖርቱ በተለይ በሩስያና ዩክሬን ጦርነት ተከትሎ ከዩክሬን ወደ ሌላው የዓለማችን ክፍል እህል ማጔጔዝ ስላልተቻለ በ10 ሚልዮኖች የሚቆጠር ህዝብ ለረሃብ አደጋ መጋለጡን አብራርቷል።

የተመድ ዋና ፀሓፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ ባለፈው ሳምንት በቪድዮ ባስተላለፉት መልእክት እንዳስጠነቀቁት ዓለማችን በምግብ እጥረት ምክንያት መቅዘፍት ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ቀውስ አጋጥሟታል ዋና ፀሓፊው የፈረንጆች ዓመት ብዙ አካባቢዎች በረሃብ አደጋ ላይ መሆናቸውን ይታወጃል ብለዋል። የሚቀጥለው የፈረንጆች ዓመትም ቢሆን በኤሽያ አፍሪካ ፣በሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ አደጋው ተባብሶ ሊቀጥል እንደሚችል ስጋታቸውን የገለፁት ጉተሬዝ በዓለማችን የሚገኙ አርሶ አደሮች በማዳበሪያና በነዳጅ ሃይል ዋጋ መጨመር ምክንያቱ ለችግር መጋለጣቸው አስረድተዋል።

በነዚህ ሃገራት የሚገኙ ህዝቦች ኮቪድ ስርጭት ያስከተለውን ጫና ለመቋቋም ጥረት ቢያደርጉም በእጃቸው ምንም ዓይነት ገንዘብ ባለመኖር የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት በመቀጠሉ የዓለም ምግብ ቀውስ…….የሚያደርጉትን ጥረት ተዳክሟል ብሏል ሪፖርቱ።

ኢትዮጵያ ናይጀሪያ፣ ደቡብ ሱዳንና የመን የረሃብ ፖለቲካ ትኩሳት የሚታይባቸው ቀውሱ መቅዘፍት ሊያስከትል ወደ ሚችል ሁኔታ እንደሚያመራ የWFP ሪፖርት ያስረዳል።

Previous articleፋሽስት የአብይ ቡድንን ጨምሮ ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ የሚጠቀሙ መንግስታት  ተጠያቂ የሚያደርግ ውሳኔ  ፀደቀ፡፡
Next articleበትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄደ ባለው ጄኖሳይድ በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥበት ዲያስፖራ ማህበረ-ሰብ  ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ ጠየቁ፡፡