Home ዜና በዓይደር ሆስፒታል በ12 ቀናት ውስጥ ብቻ በኦክስጅን አቅርቦትና  በመድሐኒት እጦት ምክንያት የ32...

በዓይደር ሆስፒታል በ12 ቀናት ውስጥ ብቻ በኦክስጅን አቅርቦትና  በመድሐኒት እጦት ምክንያት የ32 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተገለፀ፡፡

3105
0

የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ክሊኒካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ክብሮም ገ/ስላሴ በትዊተር ገፃቸው ልብ የሚሰብር ፅሁፍ አስፍረዋል፡፡

ዶ/ር ክብሮም በፅሁፋቸው በዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ባለው ከፍተኛ የመድሐኒት እጥረት ባለፉት አስራ ሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ በኦክስጅን አቅርቦት እጥረት በፀረ ባክቴርያ߹ ማደንዘዣና  በሌሎች ተዛማጅ የህክምና ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት አስራ ሁለት ህፃናት የሚገኙባቸው የሰላሳ ሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል፡፡

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን እና ወራሪ ሃይሎች በትግራይ ህዝብ ላይ ያወጁትን የጀኖሳይድ ጦርነት ተቀጥያ በሆነው ከበባና ክልከላ ምክንያት በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ስር ሆኖ በሪፈራል ደረጃ ዘርፈ ብዙ የህክምና አገልግሎቶችን ሲሰጥ የነበረው ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ሲሰጣቸው የነበሩት አብዛኞቹ አገልግሎቱን ማቆሙ የሚታወቅ ነው፡፡

እስከ አሁንም ሆስፒታሉ የሚያስፈልገው አቅርቦት ሊያገኝ አለመቻሉን ያስታወቁት ዶ/ር ክብሮም ገ/ስላሴ ይህ ደግሞ የሚያሳዝን ተግባር እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በመሆኑም አለማቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ፈጣን እርምጃ በመውሰድ በህክምና እጦት ምክንያት እየረገፈ ያለውን የትግራይ ህዝብ በመታደግ የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ ዶ/ር ክብሮም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በዊንታ ዘላለም 

Previous articleአሜሪካ ለኤርትራ ህዝብ የሰብአዊ ድጋፍ እንዳትሰጥ በአምባገነኑ ኢሳያስ አገዛዝ መከልከልዋን አስታወቀች፡፡
Next articleፋሽስት የአብይ ቡድን ለ2015 ዓ/ም በጀት አመት ያቀደውን ረቂቅ በጀት በቋፍ ያለውን ኢኮኖሚ በማባባስ  በአገሪቱ  ከፍተኛ የበጀት ጉድለት  ሊያስከትል እንደሚችል ተዘገበ፡፡