Home Uncategorized በጋምቤላ የስደተኞች መጠሊያ ጣቢያ ውስጥ ማንነቱ ባልታወቀ ታጣቂ አራት ስደተኞች መገደላቸውን የክልሉ...

በጋምቤላ የስደተኞች መጠሊያ ጣቢያ ውስጥ ማንነቱ ባልታወቀ ታጣቂ አራት ስደተኞች መገደላቸውን የክልሉ ፖሊስ  አስታወቀ፡፡

813
0

በክልሉ መርከስ በተባለው ቀበሌ ውስጥ ደግሞ በተመሳሳይ ሁኔታ ሁለት ሰላማዊያን ሰዎች በጥይት መገደላቸውን ተገልጿል፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ለ Addis standared እንደገለጹት ማንነቱ ባልታወቀ ታጣቂ የተገደሉት አራት ስደተኞች በጋምቤላ ክልል #ዲማ ወረዳ #መርከስ ቀበሌ ውስጥ በሚገኘው እና #ኦኩጎ ተብሎ በሚታወቀው የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ነው፡፡

ኦኩጎ የስደተኞች መጠሊያ ጣቢያ በጋምቤላ ደቡባዊ ክፍል የሚገኝ እና በብዛት ከደቡብ ሱዳን በማህበረሰብ በተቀሰቀሰው የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት የተሰደዱትን ስደተኞች አቅፎ የያዘ እንደሆነ የተባባሩት መንግስታት ሪፖርት አመልክቷል፣፣

የኦኩጎ የስደተኞች መጠሊያ ጣቢያ በርካታ የጎሳ ማንነት ያላቸው ስደተኞችን የያዘው ሲሆን፣አብዛኛዎቹም አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች መሆናቸውንም ተገልጿል፣፣

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ጨምረው እንዳሉት፣ በክልሉ መርከስ ቀበሌ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 10 ሰዓት ተኩል በአንድ ሞተር ብስክሌት ሲጓዙ በነበሩ ሁለት ሰላማዊያን ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ተገድለዋል፣

በፋሽስቱ የአብይ ቡድን የጥፋት መንገድ እየተመራች ያለችው ኢትዮጵያ ውስጥ በየአከባቢው በ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊያን ዜጎች የሚገደሉባት እና የሰዎች ግድያና ደም መፍሰስ በየእለቱ የሚከሰትባት ሃገር ከሆነች አራት አመታት ተቆጥረዋል፡፡

የተባባሰው የዜጎች ግድያና እልቂት በትግራይ ከታወጀው #ጀኖሳይድ ጦርነት ባሻገር በኦሮሚያ፣ #ቤንሻንጉል ጉምዝ፣ በአማራ እና በደቡብ ክልሎች በስፋት ከሚፈፀምባቸው ቦታዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ 

አማረ ኢታይ

Previous articleየአብይ ቡድን ከተወገደ በኋላ የሃገሪቱ ህዝብ የራሱን ዕድን በህዝበ ውሳኔ እንዲያረጋግጥ መሰራት እንዳለበት ተነገረ፡፡
Next articleየአሜሪካ ልኡካን የዘሄግ ውይይት