Home ዜና በጎንደር ከተማ በፅንፈኛው ፋኖ የተገደሉት የሙስሊም ማህበረ-ሰብ አባላት በተለያዩ የማህበረ-ሰብ ክፍሎች ዘንድ...

በጎንደር ከተማ በፅንፈኛው ፋኖ የተገደሉት የሙስሊም ማህበረ-ሰብ አባላት በተለያዩ የማህበረ-ሰብ ክፍሎች ዘንድ ቁጣን ቀሰቀሰ።

2015
0

በትላንትናው እለት በጐንደር ከተማ ፋኖ በተባለው ፅንፈኛ ሃይል ከ20 በላይ ሰዎች ሲገደሉ ከ150 በላይ ደግሞ ቆስለዋል፤ የተስፋፊው የአማራ ሀይል አካል የሆነው  ገዳዩ እና ጨፍጫፊው ፋኖ   በተቀነባበረ ዘዴ ጎንደር የሁከት ቀጠና በማድረግ የሙስሊም እንስቶችን በመድፈር   ንፁሃንን በመፍጀት መስጂዶችንና የሙስሊም ሃብትና ንብረትን በማውደምና በመዝረፍ ቅዱሰ ቁርዓንን  በማቃጠል  የማውድም  በታላቁ የረመዳን ፆም  የተፈፀመው  አስነዋሪ ድርጊት ጎንደር አና አዲስአበባ ጨምሮ በእምነቱ ተከታዮች ተቃውሞ እያሰተናገደ ይገኛል::

 በግጭቱ ከ20 በላይ ሰዎች መሞታቸውና ከ150 ሰዎች በላይ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የBBc ዘገባ ያስረዳል፡፡ ድርጊቱ በሙስሊም ህብረተ-ሰብ  ከፍተኛ ቁጣን እንደቀሰቀሰ ያገኘነውን መረጃ ያመለክታል፡፡

በአዲስ አበባ አንዋር መስጂድ በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚ ሰልፈኞች   በጎንደር ገዳዩ ፋኖ  በሙስሊሞች ላይ ያደረሰውን ግድያ ድምፃቸው በማሰማት አውግዘዋል::

 የአፄውን ሥርኣት ናፋቂ መቃብር ይዉረድ፤  ፋኖ ሌባ ዘራፊ ቡድን ነው፤ መንግስት የለም ወይ የሚል ምሬትም አሰምተዋል::  የአዲስ አበባውም ሆነ የአማራ የእስልምና ጉደዮች ከፍተኛ ም/ቤቶች ጥቃት የፈፀሙት አካለት ለፍርድ  እንዲቀርቡ ጠይቀዋል፡፡

 oromia media network  የጎንደር ከተማ ነዋሪዎችን በማነጋገር አገኘሁት ባለው መረጃ    እሯሱ በራሱ ፈራጅ የሆነው ተሰፋፊው የአማራ ሀይል  ተበድያለሁ ያለውን የሙስሊም ማህብረ-ሰብን ከመካስ ይልቅ ነገሩን ለማደባበስ ሳይሆንለት ሲቀር  ደግሞ አታራግቡ ሲል መውቀሱን ገልፀዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በጎንደር ከተማ የሙሰሊም ማህበረ-ሰቡ ወጥቶ ለመግባት አዳጋች እንደሆነበትም መረጃው ያስረዳል::

በፋሽስቱ ቡድን  ድጐማ  ሀገር የሚያተራምሰው  የፋኖ ቡድን  በተለያዩ ስያሜዎች  ተደራጅቶ ከጎንደር እስከ ደሴ  ከሚሴ  እና ወለጋ  ግድያና አፈና ማካሄድ መለያ ባህሪው  ቢሆንም  ቤንሻንጉል ጉሙዝ ጉባ ላይ የሰው ህይወት በቁሙ ማቃጠሉም በታሪክ መቼም የሚረሳ አይደለም:: 

 የጎንደሩ የትላንት በስትያ ትርምስ እና ሁከት ተከትሎ በርካታ ሀሳቦች እየተንሸራሸሩ ነው፤ የጎንድሩ የንፁሃን ሙስሊሞች ግድያ ከእነ ህይወታቸው በእሷት የተለበለቡ ሚስኲን የትግራይ ወገኖችን ሲያስታውስ  የመስጂዶቹ መቃጠል  ቅዱስ ቁርአኑ መራከስ  የኢትዮዽያ የክርስትና ሆነ የእስልምና እምነት መሰረት የሆነችው የአክሱም ማርያም ፅዮን እና አል ነጃሺ ቅዱስ ስፍራ መገኛዋ ትግራይ ላይ የተፈፀመው ጀኖሳይድ መቋጫው የት ይሆን የሚለውንን ጥያቄ ማጫሩ ግድ  ሆኗል::  

Previous articleበትግራይ የጀኖሳይድ ጦርነት የክልሉን በጤና ስርዓት ውድመት
Next articleየማህብራዊ ሚድያ ውሎ፡፡