Home ዜና በፋሸስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ  የፌደራል ተቋማት ሰራተኞች ችግር ላይ መውደቃቸው ለ አፍሪካ...

በፋሸስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ  የፌደራል ተቋማት ሰራተኞች ችግር ላይ መውደቃቸው ለ አፍሪካ ሰብዓዊ መብቶች  ኮሚሽን ክስ አቀረቡ፡፡

822
0

ፋሸስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ በፈፀመው የጀኖሳይድ ጦርነትና ባኖረው ከበባና ክልከላ ተከትሎ በትግራይ በሚገኙ 36ፌደራል ተቋማት  ከ104 ሺ በላይ የተቋማቱ ሰራተኞች ወርሃዊ ደሞዝና ሌሎች አገልግሎት ማግኘት ባለመቻሉ ትልቅ ችግር ውስጥ መግባታቸው ተከትሎ የትግራይ ዩኒቨርስቲዎቸ መሁራን ማህበር፣ ከትግራይ ሰብዓዊ መብቶች ተማጋች ሲቪል ማህበረ-ሰብ ጥምረት ጋር በመተባበር፤ የህግ ባለሙያዎችን በማቋቋም በተወካዮቻቸው በኩል ግንቦት 27 ቀን 2014 ዓ.ም ወደ አፍሪካ ሰብዓዊ መብቶች  ኮሚሽን ክስ ማቅረባቸው  በተቋማቱ የተወከሉ የህግ ባለሙያዎች በሰጡት ማብራርያ ገልፀዋል፡፡

 በቀረበው የክስ ዝርዝር ውስጥ የተቋሙን የክስ አንቀፆችን በመጥቀስ በክሱ ላይ የቀረቡ ዝርዝሮችን በመግለፅ ከነዚህም ፋሸስቱ ቡድን ባኖረው ከበባና ክልከላ በ36ቱ የፌደራል ተቋማት ሰራተኞች ደመወዝ አለመከፈላቸው፣ ምንም ዓይነት ህዝባዊ አገልግሎቶች ማግኘት እንዳልቻሉና ሌሎች ሃሳቦችን በማንሳት በአጠቃላይ በተፈጠረው ችግር ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ስነ-ልቦናዊ ችግር ማጋጠሙን ኣክለዋል፡፡

ወደ አፍሪካ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ክስ ለማቅረብ ሲታሰብ መማላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች እንዳሉ የተገለፀ ሲሆን እነዚህ ተቋማትም ቅድመ ሁኔታውን በማማላት ክስ ማቅረባቸውም የህግ ባለሙያዎች ኣብራርተዋል፡፡

ስለሆነም ይላሉ በተቋማቱ የተወከሉ የህግ ባለሙያዎች፣ በቀረበው ዝርዝር ክስ ላይ Africa human rights comussion በአትኩሮት በመመልከት በአፋጣኝ መፍትሄ መስጠት እንዳለበትም ጠቁሟል፡፡

በመጨረሻም እንደዚህ ኣይነት ወንጀል በመፈፀም ከህግ ማምለጥ እንደማይቻልና ተጠያቂነት እንደሚረጋገጥ በመግለፅ ችግሮች እስኪቀረፉ የተጀመረው ሂደት ቀጣይ እንደሚሆንም ገልፀዋል፡፡

በተቋማቱ የተወከሉ የህግ ባለሙያዎች ፣ በቀረበው ዝርዝር ክስ ላይ የአፍሪካ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በአትኩሮት በመመልከት በአፋጣኝ መፍትሄ መስጠት እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡

መዓዛ መኮነን

Previous articleሶስተኛዉ ዙር የትግራይ ህዝብ የመመከት እንቅስቃሴ በትግራይ የዲያሰፖራ ማህበረ-ሰብ በተለያዩ ሀገራት  ተጠናክሮ ቀጥለዋል ፡፡
Next articleየ2021 የአለም የእርሻ ሽልማት የሎሬትነት ማእረግን፤ ሎሬት ፕሮፌሰር ምትኩ ሃይለ በመቐለ  እውቅና አሰጣጥ መድረክ ተከናወነ፡፡