Home ዜና ባለፉት የኢህአዲግ ዘመን የተሰሩት ሰፊ የልማትና የዴሞክራሲ  ስራዎች  አገሪቱን ወደ ፊት እንድትራመድ...

ባለፉት የኢህአዲግ ዘመን የተሰሩት ሰፊ የልማትና የዴሞክራሲ  ስራዎች  አገሪቱን ወደ ፊት እንድትራመድ ከማስቻሉም ባሻገር ሰላሟንና ፀጥታዋ የተረጋገጠ ለሌሎችም የሰላም ተምሳሌት በመሆን ስሟ በዓለም መድረክ  የምትጠራ ሆኗ ዘልቃለች፡፡

898
0

ይሁንና  ካለፉት አራት ዓመት ጀምሮ በግርግር ወደ ስልጣን የመጣው ፋሸስቱ የአብይ በድን ይህንኑ ዓለም የመሰከረለትን የሰኬት ጎዳና ሽምጥጥ አድርጎ ሲክድ ብዙዎቹም እሱን ተከትለው የጨለማ ወቅት ብለው  ሲደግፉ ና ሲያንጨበጭቡ ተሰምተዋል፡፡

ታዲያ ይህ  ከፋሽሽቱ የግል የጥላቻ ስሜት ፣አመለካከት ና  ጭፍን አስተሳሰብ የመነጨ እንጂ   በአገሪቱ የተመዘገበው ለውጥስ የአደባባይ ሃቅ ነው  የሚሉት  አንዳንደ ያነጋገርናቸው የመቀለ ይንቨርስቲ ምሁራን ዶ/ር ተኽላይ ተስፋይና ብርሃነ ዘሚኪኤል ፡፡

ይልቁንስ   በአለፉት አራት አመታት በፋሽስቱ የአብይ ቡድን  መሪነት  የታዩ ህገወጥ የፀረ ልማት እንቅስቃሴዎች  በትክክል  ፋሽስቱ የተጠቀመበት አገላለፅ  በተግባር ያስመሰከረበት ወቅት እንደሆነ ነው ምሁራኑ የሚናገሩት፡፡

በታላቅነቷ ብዙ የሚዘመርላት ኢትዮጵያን ከፋሸስቱ የአገዛዝ ስርዓት ከማላቀቅና ከወረደችበት የቁልቁለት ጉዞ ከማውጣት ዝምታን የመረጡ ዜጎቿ አስከ መቼ የሚለውን ጥያቄ  የብዙዎች ጥያቄ ነው፡፡

ይህን ጥያቄ የቆረቆራቸው ኢትዮጵያውያን ካሉ ጊዜው አሁን መሆኑ በመገንዘብ ይህንን ስርአት በቃህ ሊሉት እንደሚገባና ለመብታቸው ከሚታገሉ ሃይሎች ጎራ በመቀለቀል  አገሪቷን ከመበታተን  አደጋ ለመታደግ  የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ የምሁራኑ አስተያየት ነው ፡፡

ፉርቱና ገብሩ

Previous articleኢትዮጵያ የግጭቾች መነሃሪያ መሆንዋን የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ እርዳታ  UN, OCHA ባወጣው ሪፖርት ይፋ አድርገ፡፡
Next articleሶስተኛዉ ዙር የትግራይ ህዝብ የመመከት እንቅስቃሴ በትግራይ የዲያሰፖራ ማህበረ-ሰብ በተለያዩ ሀገራት  ተጠናክሮ ቀጥለዋል ፡፡