Home ዜና ትክክለኛና ሃቀኛ ብሄራዊ እርቅ ከመጣ ለመደገፍና ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸው ፕሮፌሰር  መረራ  ጉዲና...

ትክክለኛና ሃቀኛ ብሄራዊ እርቅ ከመጣ ለመደገፍና ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸው ፕሮፌሰር  መረራ  ጉዲና ተናገሩ፡፡

979
0

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በሚከተለው የተሳሳተ አቅጣጫ ሃገሪቱ ወደ ፊት የመራመድ ዕድል የላትም ሲሉ የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ተናገሩ፡፡ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የሃገሪቱ ሁለንተናዊ ቀውስ መፍትሄ ለማፈላለግ ሁሉን አካታች ድርድር ማካሄድ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ሃገራዊ ውይይት ተደርጎ ኢትዮጵያ ከተጋረጠባት አደጋ እንታደግ ሲሉ ይመጉቱ የነበሩት አንጋፋው ፖለቲካኛና የኦሮሞ ፌራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ ሊቀ መንበር ፕ/ር መረራ ጉዲና የፋሽስቱ ቡድን ተቀናቃኝ ፖለቲከኞችን እስር-ቤት አጉሮ  የምርጫ ቦርድ ሃላፊዋ የቡድኑ የቀን እጁ ሆና ሙሉ በሙሉ በተጠመዘዘው ምርጫ አንሳተፍም ማለታቸው አይዘነጋም፡፡

በፋሸስቱ ቡድን አመራርነት የመበታተን ቋፍ ላይ የደረሰችው ኢትዮጵያ የፓርቲያቸው ዳግም ትንሳኤ ከሆነው ድርጅታዊ ጉባኤ በኋላ ቃለ መጠየቅ ሲሰጡ የመጀመሪያ መሆኑ ነው’ ፕ/ር መረራ ጉዲና ከOMN ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ የፋሽስቱ አብይ ቡድን ያደራጁት ሃገራዊ የምክክር ኮምሽን እንኳን የታጠቀ ለኛም መቀበል ይከብዳል በማለት በሃቅ የመደራደር ጥያቄ ውስጥ ካልገባን ሃገሪቱ ወደ ፊት መራመድ እንደማይትችል ይገልፃሉ፡፡

የአብይ ቡድን በድርጅታቸው አባላት ላይ ጭቆናና እንግልት እያደረሰ በመሆኑ የፓርላማ አባል የነበሩት የኦፌኮ አባላትን ጨምሮ ትግልን በመምረጥ ወደ ኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እየተቀላቀሉ መሆናቸውን የገለፁት ፕ/ር መረራ ጉዲና አብይና ስብስቡ ግትር የሆነ አቋሙን ትቶ ሁሉን ያካተተ ድርድር ሊካሄድ እንደሚገባ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ሃገር ገንቢና ሃገር አፍራሽ እየተባለ ቡዙ ዓመታት ያለፉ መሆናቸውን ያብራሩት ፕ/ር መረራ፣ አብይና ስብስቡ በሚከተሉት የተሳከረ አስተሳሰብ ሃገሪቱን በእጅጉ የሚጎዳ መሆኑን ገልፀው ትክክለኛና ሃቀኛ ብሄራዊ እርቅ ከመጣ ለመደገፍና ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውም አስታውቀዋል፡፡     

Previous articleየኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መግለጫ
Next articleበትግራይ ተወላጆች ላይ  ያነጣጠረ የጥላቻ ንግግር ስርጭትን ለመግታት የትግራይ ምሁራንና ባለሙያዎች ማህበረሰብ እየሰራ ነው