Home ዜና ትግራይ የውጪ ጉዳዮች ጽ/ቤትየአጣሪ ኮሚሽኑ አካሄድ  ግፍ ለደረሰበት የትግራይ  ህዝብ ፍትህ የሚያረጋግጥ...

ትግራይ የውጪ ጉዳዮች ጽ/ቤትየአጣሪ ኮሚሽኑ አካሄድ  ግፍ ለደረሰበት የትግራይ  ህዝብ ፍትህ የሚያረጋግጥ መሆን ይገባዋል አለ፡፡

726
0

የተመድ አለምአቀፍ አጣሪ ኮሚሽን የትግራይን ህዝብ ጥቅም ግምት ውሰጥ ያላስገባ በተናጠል ከፋሽስቱ የአብይ ቡድን ጋር የሚያደርገውን ትብብር የትግራይ መንግስት ከኮሚሽኑ ጋር ላለመተባበር በቂ ምክንያት እንደሚሆነው የትግራይ የውጪ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

መንግስት በትግራይ ህዝብ የተፈጸሙ የጀኖሳይድ ወንጀሎችን በተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በተቀቋመው ገለልተኛ የአጣሪ ቡድን ለሚካሄደው የምርመራ ስራ ስኬት ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ ቢሆንም የኮሚሽኑ አካሄድ ግን ግፍ ለደረሰበት የትግራይ  ህዝብ ፍትህ የሚያረጋግጥ አይደለም ብሏል፡፡

የትግራይ የውጪ ጉዳዮች ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ፣ በፋሽስቱ የአብይ ቡድን እና ግብረአበሮቹ የተፈጸሙትን እና እየተፈጸሙ የሚገኙ ዘግናኝ ወንጀሎችን በገለልተኛ የአጣሪ ቡድን እንዲጣራ የትግራይ መንግስት ሁሌም ቁርጠኛ ነው ብሏል፡፡

የአጣሪ ኮሚሽኑ  ከትግራይ መንግስት ጋር ለሚያደርገው ግንኙነት  ምክንታዊ ባልሆነ መንገድ መዘግየቱ እንዳሳሰበው የገለታ መግለጫው 

ቀደም ሲል በሂዩማን ራይትስ ዎችና አምኔስቲ ኢንተርናሽናል ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጓች  ድርጅቶች እና በነፃ የሚድያ ተቋማት በትግራይ ህዘብ ላይ በፋሽስቱ ቡድንና ግብረ አበሮቹ የተፈጸሙና እየተፈጸሙ የሚገኙ ወንጀሎችን በሚገባ ተሰንዷል ያለው የጽ/ቤቱ መግለጫ ወራሪ ሃይሎች የጦርነት ወንጀሎችና በሰብአዊ ፍጡር  ላይ ያነጣጠረ ወንጀል ስለመፈጸማቸው ማረጋገጣቸውንም አስታውሷል፡፡

በፋሽስቱ ቡድንና ግብረ አበሮቹ በትግራይ ህዝብ ላይ ጫፍ የረገጠ የጀኖሳይድ ወንጀል እንደፈጸሙባት ያስታወሰው መግለጫው፣ የትግራይ መንግስት መርህን መሰረት ባደረገ መልኩ የአጣሪ ቡድኑ  ተልእኮ ዳር እንዲደርስ አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

የፋሽስቱ ቡድን ባለስልጣናት የአጣሪ ቡድኑ በሚያካሂደው የማጣራት ስራ ለመቆጣጠርና በሂደቱ ላይ እንዲሳተፉ  ለማድረግ እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው ያለው የጽ/ቤቱ መግለጫ፣ድርጊቱ የአጣሪ ቡድኑ ተአማኒነትና ነጻነትን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባው ነው ብሏል፡፡

የተቋቋመው ገለልተኛ የአጣሩ ቡድን እንደ ገለልተኛ ተቋም የምርመራ ስራውን ራሱን በገለልተኛነት ማከናወን ይገባዋል ብሏል መግለጫው፤

 የሰብአዊ መብት ከፍተና ኮሚሽነር ፅ/ቤት ስራ የትግራይ መንግስት የሚያደንቅ ቢሆንም በወንጀሉ ተጠያቂ ከሆነው የፋሽስቱ የአብይ ቡድን ጋር በጋራ የማጣራት ስራውን ለማካሄድ  የወሰነውን ውሳኔ ግን አፍራሽና ፍትህ እንዳይረጋገጥ ጋሬጣ መሆኑን አብራርቷል መግለጫው፤

የፋሽስቱ አብይ ቡድንና የአገር ውስጥ ተላለኪዎቹ  በማጣራት ሂደቱ እንዲሳተፉ ማድረግ ግን የቡዱኑ ተልእኮ እንደመክሸፍ ይቆጠራል ያለው መግለጫው፤ ይህም ትርጉም የለሽ ሃሳብ መሆኑን ገልጿል፡፡ የፋሽስቱ ቡድን ባለስልጣናት በአጣሪው ቡድን እንዲጣራ የሚፈልጉት በፈረንጆቹ አቆጣጠር እስከ ሰኔ ወር 2021 የታዩ ክስቶቶች ብቻ ናቸው ያለው የጽ/ቤቱ መግለጫ ይህም የፋሽስቱ የፖለቲካ ፍላጎት ብቻ የሚያሟላና የሂደቱም ትኩረት ከትግራይ ውጪ ባሉ አከባቢዎች

Previous articleበተመድ የተቋቋመው ኮሚሽን ገለልተኛ በመሆን በአስቸኳይ አጣርቶ ወንጀለኞች ወደ አለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንዲያቀረብ  ጥሪ ቀረበ፡፡
Next articleየትግራይ ሴንተራል ኮማንድ አባል አቶ ጌታዉ ረዳ  ሶስተኛዉ ዙር  የዲያስፖራ የመመከት ዘመቻ በድል እንዲጠናቀቅ   ጥሪ አቀረቡ፡፡