Home ዜና አሜሪካ ከ500 በላይ ወታደሮቿን ዳግም  ወደ ሶማልያ ለመላክ ማቀዷ ለአዲሱ ፕሬዝዳንት ያላትን...

አሜሪካ ከ500 በላይ ወታደሮቿን ዳግም  ወደ ሶማልያ ለመላክ ማቀዷ ለአዲሱ ፕሬዝዳንት ያላትን ድጋፍ   የሚያሳይ ነው ሲል BBC ዘገበ፡፡

845
0

ኣሜሪካ ጦሯን ወደ ሶማልያ ለመላክ መወሰኗ የትራምፕ ኣስተደደር የሚቀለብስ ውሳኔ ነው ሲል ዘገባው አመላክቷል፤ BBC አሜሪካ ለምን ጦርዋን በድጋሚ ወደ ሶማሊያ መላክ ፈለገች በሚል ርእስ ይዞት በወጣው ዘገባ በተሸናፊው የሶማልያ ፕሬዝደንት ሞሓመድ ኣብዱላሂ ፈርማጆ መንግስትና በቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር መካከል የነበረው አለመግባባት አሜሪካ ወታደሮቿን ከሶማልያ እንድታስወጣ ምክንያት ሆኗታል ብሏል፡፡

አሜሪካ ኣሁን ደግሞ ጦሯን ወደ ሶማልያ ለመላክ መወሰንዋ በመግለፅ የትራምፕ አስተደደር ውሳኔ የሚቀለብስ ነው ሲል ዘገባው አስፍሯል፡፡

ይህ የአሜሪካ ውሳኔ የዩኤስ ኣፍሪካ ኮማንድ /ኣፍሪኮም/ በሶማልያ አነስተኛ ቁጥር ያለው ጦር ማሰማራቷ የእስላማዊ ታጣቂዎች ጥቃት ለጨመረባት ሶማልያ እረፍት የሚሰጥ ነው ብሏል ዘገባው፡፡

የትራምፕ ውሳኔ ተከትሎ የተፈጠረውን የደህንነት ክፍተት ለመሙላት ከጁቡቲ በመነሳት ወደ ሶማልያ ገብተው ለሚወጡ የአሜሪካ ወታደሮቸም ስራ የሚያቀል እንደሆነ Africom ገልፃል፡፡

የአሜሪካ ጦር ከሶማሊያ መውጣቱን ተከተሎ በሶማለያ ጥቋቶች ተበራክታል ያለው the Africa center for strategic  ጦሩ  መውጣትን ተከትሎ በነበረው ዓመት በአልሸባብ የደረሱት ጥቃቶች ከ1771 ወደ 2072 አድገዋል፡፡

ከፀጥታ አካላት ጋር የሚደረጉ ውጊያዎቸ በ32 በመቶ ከፍ ብላል ያለው የ BBC ዘገባ ባለፈው ወር ብቻ 450 የሚደርሱ የአልሸባብ ተዋጊዎች በደቡብ ሶማለያ የሚገኘውን የአፍሪካ ህብረት ካምፕ በማጥቃት 40 የብሩንዲ ወታደሮች  መገድላቸው በዘገባወ አስፍራል፡፡

የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ሶማልያ መመለሳቸው ትልቅ ለውጥ ያመጣል የሚሉት መቀመጫቸው በሞቃዲሾ የሆነውና በደህንት ላይ የሚያተኩረው heral strategic ዳይሬክተር የሆኑት #ሳሚራ ጋይድ ጦርነቱ ማሸነፈ ባያሰችልም እንኳ ለአዲሱ አስተዳደር ደህንነት ቅደመ ሁኔታዎችን እንዲያመቻች እድል ይሰጣል ማለታቸውን BBC ዘግቧል፡፡

ወደ ሶማሊያ የሚመጣው የአሜሪካ ጦር በርካታ የአልሸባብ አመራሮንን ኢላማ ያደረገ ሃላፊነት አለው ያለው የ BBC ዘገባ ቀደም ሲል የተደረጉ የአሜሪካ  የአየር ጥቃቶች የቡዱኑ እንቅስቋሴ ማስተጋጎሉንና መሪዎቹም እንደልብ እንዳይንቀሳቀሱ እና ታጣቂዎቹም ትላልቅ ጥቃቶችን እንዳይፈፅሙ ማገዱን ዘገባው አስታውሷል፡፡

መአዛ መኮነን

Previous articleየዓፋር ህዝብ ከፍተኛ ግፍ እየተፈፀመበት መሆኑ የአፋር ፌዴራሊስት ሃይሎች አመራር ገለፁ።
Next articleየፋሽስቱ የአብይ ቡድን ሰራዊት በምስራቅ ሸዋ ዞን በቦሰት ወረዳ በህጻናት ላይ ግድያና አፈና አካሄደ።