Home Uncategorized አዲስ አበባ ውስጥ የተስፋፋው ዝርፊያና ያስከተለው ስጋት

አዲስ አበባ ውስጥ የተስፋፋው ዝርፊያና ያስከተለው ስጋት

834
0

—-

በአዲስ አበባ ግድያዎችና የስርቆት ወንጀሎች በመበራከቱ በግል የትራንስፖርት አገልግሎት የተሰማሩ አካላት ችግር ላይ መውደቃቸው አዲስ ስታንዳርድ ዘገበ።

በአዲስ አበባ በነዚህ በግል የትራንስፖርት አገልግሎት የተሰማሩ ወገኖች ላይ ያነጣጠረ ግድያና ስርቆት ምክንያት 6 አሽከርካሪዎች መገደላቸው በዚሁ ሓምሌ ወር በ15 ቀን ብቻ የሰሌዳ ቁጥራቸው ኮድ 3 የሆኑ ዘጠኝ ተሽከርካሪዎች መዘረፋቸው አዲስ ስታንዳርስ ዘግቧል።

በዚሁ የተነሳ የሰሌዳ ቁጥር 3 አሽከርካሪዎች ሞት ያበቃና የዳረገ መንግስት ከለላ ሊሆነን ይገባል የሚሉ መፈክሮችን ይዘው ሰላማዊ ሰልፍ መውጣታቸው ይሄው የአዲስ ስታንዳርድ ዘገባ ያስረዳል። አሽከርካሪዎቹ ተሳፋሪ መስለው በሚቀርቡ ወረበሎች በቢላ ተወግተው በገመድ ታንቀው እንደሚገደሉና ንብረቶቻቸው እንደሚዘረፉ የአዲስ ስታንዳርድ ዘገባ ያመለክታል። አስተያየታቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ የሰጡ አንዳንድ የታክሲ አሽከርካሪዎች ከዚሁ የግድያና የስርቆት ተግባር ራሳቸውን ለማትረፍ በዋና ዋና ጎዳናዎች ብቻ ተወስነው አገልግሎት ለመስጠት እንደወሰኑና ማታ ማታ ላለመሥራት መገደዳቸው አስታውቀዋል።

  

Previous articleየወላይታ እና የጉራጌ ህዝብ በክልል የመደራጀት መብት እንዲከበር  ለጠየቁት ጥያቄ በፋሽስቱ የአብይ  ቡድን   ክልል የመሆን  ጥያቄያቸው መነፈጉን  ተገለፀ ፡፡
Next articleላለፉት 30 ዓመታት የትግራይ ህዝብ በላቡና በጉልበቱ ያለማውን የደን ሀብቱን የፋሽስቱ ቡድን ና ግብረኣበሮቹ ኣስበውና ኣልመው በትግራይ ህዝብ ላይ በከፈቱት የጀኖሳይድ ጦርነት ምክንያት እንዲወድሙ  ሆነዋል ፡፡ ይሁንና  በትግራይ ህዝብ ጠላቶቸ የወደሙትን ደኖችና እጽዋቶችን ከክረምት መምጣት ጋር ተያይዞ  መልሶ ለማልማት በማቀድም  በክልሉ በተለያዩ ኣካባቢዎች የችግኝ ተከላ እየተከናወኑ የገኛሉ ፡፡