Home ዜና ኢትዮጵያውያን እናቶች እንደ ሶማሊያውያን እናቶች በትግራይ ጦርነት  የሄዱ ልጆቻችን የት ገቡ ብለው...

ኢትዮጵያውያን እናቶች እንደ ሶማሊያውያን እናቶች በትግራይ ጦርነት  የሄዱ ልጆቻችን የት ገቡ ብለው ሊጠይቁ ይገባል ሲሉ ምሁራን ገለጹ፡፡

848
0

የሶማሊያ እናቶች የሶማሊያ ወታደሮች በኢሳያስ ጋባዥነትና በአብይ ይሁንታ በትግራይ ጦርነት እንደተሳተፉ ሲያውቁ ልጆቻችን የት ገቡ? ለምን? በማይመለከታቸው ጦርነት ገቡ? በማለት በሰለማዊ ሰልፍና በምክር ቤት ሳይቀር ፋርማጆን እንዳፋጠጡት ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያውያን እናቶች ግን ልጆቻቸው ወደ አላስፈላጊ ጦርነት ሲገቡ ለምን ብለው አልጠየቁም፤ በተለይ ደግሞ ምሁራን የሃይማኖት አባቶችና ታዋቂ ግለሰቦች የጦርነት አስከፊነት በመገንዘብ ለሰላም ከመስበክ ይልቅ የትግራይ ጦርነት እንዲባባስ የላቀ ሚና እንደነበራቸው  የህግ ምሁር አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ይናገራሉ፡፡

በመቐለ ዩኒቨርሲሰቲ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር አቶ ገዛኢ ደስታ በበኩላቸው ፋሽስቱ አብይ አሕመድ ከህግና ስርአት ውጭ መንበረ ስልጣኑን በሃይል እንደተቆጣጠረ ገልጸው አሁን ላይ ስርአቱ በመውደቅ ላይ ያለ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

ሶማሊያሊውያን  ምርጫ በሚያደርጉበት ወቅት ፋሽስቱ አብይና አምባገነኑ ኢሳያስ ፋርማጆን እንዲመረጥ የተለያዩ ሴራዎች ቢጎነጉንም በሶማሊያውያን ከሽፏል፤ አዲሱ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼህ መሃመድ  ሲያሸንፉ አምባገነኖቹ ራስ ምታት ሆኖባቸዋል ያሉት ምሁራኑ ስልጣን ያሉ አምባገነኖች ለማስወገድና ሰላም ለማስፈን ትብብር ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሶማልያውያን ያለ ምንም ተጽእኖ መብታቸውን ተጠቅመው የሚበጃቸውን መሪ መምረጣቸቸውን ለሰላም ያላቸው አቋም ያሳያል ያሉት ምሁራኑ ኢትዮጵያውያን በተለይ የኢትዮጵያ እናቶች ልክ እንደ ሶማሊያውያን እናቶች ልጆቻችን የት ገቡ ብለው ሊጠይቁ ይገባል ብለዋል፡፡

ለላፉት አራት አመታት የአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ጸጥታ እጦት እና ትርምስ አምባገነኑ ኢሳያስ አፈወርቂ ፋሽስቱ ቡድን መሪ አብይ አሕመድ እና የቀድሞ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ፋርማጆ የጥፋት ስምምነት መሆኑን የገለጹት ምሁራኑ  ሶስቱ  መሪዎች ምርጫ፤ ህግና ስርአትን  የሚጠየፉ እንዲሁም የዜጎች መብት በመደፍጠጥ በጦርነትና ግርግር ውስጥ በሃይል ስልጣናቸውን ማራዘም የሚፈልጉ አምባገነኖች እንደሆኑም አስረድተዋል፡፡

ወ/ሚካኤል  ገ/መድህን

Previous articleፋሽስቱ የአብይ ቡድን በጋዜጠኞች ላይ እየፈፀመው ያለውን አፈናና እስራት ተጠናክሮ መቀጠሉን የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚድያዎች ዘገቡ፡፡
Next articleወራሪ የኢሳያስ ሰራዊት በሰሜን ምዕራብ ትግራይ የከፈተው ጥቃት በጀግናው የትግራይ ሰራዊት ከሸፈ