Home Uncategorized እጅግ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ ተገድሎ ወደ ተከዜ ወንዝ የተጣለ የአንድ የትግራይ ተወላጅ...

እጅግ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ ተገድሎ ወደ ተከዜ ወንዝ የተጣለ የአንድ የትግራይ ተወላጅ አስከሬን መገኘቱን ተዘገበ፡፡

1665
0

—-

በምዕራብ ትግራይ በወራሪዎች ተገድሎ የተቃጠለ የሰው አስከሬን ወደ ተከዘ ወንዝ የተጣለ መገኘቱን በስፍራው ከነበሩ የዓይን ምስክሮች በማረጋገጥ ትግራይ ሚድያ ሃውስ ዘግበዋል፡፡

የትግራይ ሚድያ ሃውስ ሪፖርተር በስፍራው ተገኝቶ እንደዘገበው የተከዜ ወንዝ ገባር በሆነውና በሱዳን ድንበር ላይ በሚገኘው ሰቲት ወንዝ ተብሎ በሚጠራ ወንዝ ውስጥ የተገኘው አስከሬን ሁኔታ ከዚህ በፊት ከተገኙ የተጋሩ አስከሬኖች አገዳደል እጅግ ዘግናኝና የተለየ መሆኑን የዓይን ምስክሮቹ ተናግረዋል፡፡

በሱዳናዊያን ዓሳ አስጋሪዎችና በአከባቢው በሚገኙ የትግራይ ተወላጅ ስደተኞች ተገኝቶ እንዲወጣ የተደረገው አስከሬን ገላው ሙሉ በሙሉ የተቃጠለ፣ በአንድ ጉኑ ላይ በስለት የተበሳና ብልቱ የተቆረጠ መሆኑን በስፍራው ተገኝተው አስከሬኑን ከወንዝ ካወጡት ሱዳናዊያን አንዱ የሆነው ኢብራሂም ሲዒድ በዚህ መልኩ ይገልጿል፡፡

“ባለፈው ዓመት በትግራይ ምዕራባዊ ዞን የሚኖሩ ተጋሩ በተስፋፊው የአማራ ታጣቂዎችና ፍጹም ጭካኔ በተሞላው  በገዳይ የፋኖ የአማራ ቡድን በጅምላ እየተጨፈጨፉና በጭካኔ እየተገደሉ ወደ ተከዘ ወንዝ እየተወረወሩ እንደቆዩና በሱዳን ድንበር አከባቢዎች አስከሬናቸው እየተለቀሙ እንደሚቀበሩ እየተደረገ መቆየቱንም የትግራይ ሚድያ ሃውስ  በዘገባው አስታውሷል፡፡”

ባለፈው ዓመት በምዕራብ ትግራይ ህዝብ ላይ በተስፋፊው የአማራ ታጣቂ ሃይሎች በደረሱ ጭፍጨፋዎች የተገደሉ ተጋሩ አስከሬናቸው አንዳንዶችም እጆቻቸውን በፊጥኝ ታስረው፣ ከፊሎቹ ደግሞ እግሮቻቸውና እጆቻቸውን ተቆርጦ በተከዘ ወንዝ ውስጥ እንዲጣሉ ሲደረግ እንደነበርም ነው ዘገባው ያመላከተው፡፡

ባለፈው ዓመት ብቻ የ120 የትግራይ ተወላጆች አስከሬኖች ከተከዘ ወንዝ ተለቅሞ በጅምላ እንዲቀበር መደረጉን በስፍራው የተጋሩ አስከሬረን ዝርዝር እየከተበ የሚይዘው እና ገብረተንሳይ የተባለ አረጋግጧል፡፡

“አስከሬኑ ሦስት አራት ችግሮች የሚታይበት ነው፤ ሰውነቱ ሙሉ በሙሉ በእሳት ተቃጥሏል፤ የሰውነቱ ግራ ጎን በስለት ተወግቷል፤ ሦስተኛማ ዘግናኝ የሚያደርገው ደግሞ ብልቱን ተቆርጣል፡፡ 

አስከሬኑ ያገኘነው እዚህ ወንዝ ውስጥ ነው፤ እንዲህ ዓይነት ዘግናኝ ሁኔታ ከዚህ በፊት አይቼ አላውቅም፤ ሁኔታው በጣም ያማል፡፡

እግሮቻቸው የተቆረጡ፤ እጆቻቸው የተቆረጡ 10 የሚሆኑ የተጋሩ አስከሬን እዚህ ማዶ ላይ ቀብረናቸዋል፤ ዛሬም ልክ እንደ አምና ሙሉ ሰውነቱ የተቃጠለው እና ብልቱ የተቆረጠው አንድ አስከሬን እየቀበርን ነን፤ አምና 126 የትግራይ ተወላጅ አስከሬኖች በተከዜ ወንዝ ተጥለው በጎርፍ እዚሁ በመልቀም ቀብረናቸዋል፤ እነሱም እጆቻቸውን የፊጥኝ የታሰሩ ሌላ አካላቸው የተጉዳ ነበር፤ ሁኔታው እጅግ አሰቃቂ ነበር፤ ዛሬም የበሳ ነው በጣም የሚያሳዝን ነው ትግራዋይ በዚህ መሬት እንዳይኖር የተስፋፊው የአማራ ኢሊት ውጤት ነው፡፡”

አማረ ኢታይ

Previous articleየዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሓኖም ከካዛኪስታን ብሄራዊ የህክምና ሳይንስ ዩኒቨርስቲ የክብር የፕሮፌሰርነት ማአረግ ተበረከተላቸው፡፡
Next articleበሱዳን መጠልያ ካምፕ በከባድ የማህበረ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ ስደተኞች ላይ እያጋጠማቸው  ያለውን ችግር በአስቸኳይ እንዲፈታላቸው የአሜሪካ የሰኔትና ኮንግረስ አባላት ኣሳስበዋል፡፡