Home ዜና ወራሪ የኢሳያስ ሰራዊት በሰሜን ምዕራብ ትግራይ የከፈተው ጥቃት በጀግናው የትግራይ ሰራዊት ከሸፈ

ወራሪ የኢሳያስ ሰራዊት በሰሜን ምዕራብ ትግራይ የከፈተው ጥቃት በጀግናው የትግራይ ሰራዊት ከሸፈ

1845
0

ወራሪውና ፋሽስቱ የኢሳያስ ሰራዊት ግንቦት 16, 2014 ዓ/ም በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ልዩ ስሙ ገዛ ጊሌ የሚባል ከባቢ አጥቅቶ ለመያዝ ሁለት ብርጌድና አንድ ሻለቃ አሰማርቶ የከፈተው ጥቃት በጀግናው የትግራይ ሰራዊት ከሸፈ።

የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ እንዳስታወቀው ጀግናው የትግራይ ሰራዊት በወሰደው የመከላከልና ፀረ ማጥቃት እርምጃ አንድ የበርጌድ አዛዥ፣ ሶስት የሻለቃ አዛዥ ጨምሮ ከ300 መቶ በላይ የወራሪው ሰራዊት ተደምሰሷል።

ድሽቃ፣ ወታደራዊ የሬድዮ መገናኛ ጨምሮ በርካታ ቀላልና ከባድ የጦር መሳሪያ ተማርኳል።

አረመኔያው የኢሳያስ ሰራዊት የደረሰበትን ምት ተከትሎ ግንቦት 21 እና 22/2014 ዓ.ም የሸራሮ ከተማን በከባድ መሳሪያ በመደብደብ ሰላማዊ ዜጐች ላይ ጉዳት አድርሷል።

Previous articleኢትዮጵያውያን እናቶች እንደ ሶማሊያውያን እናቶች በትግራይ ጦርነት  የሄዱ ልጆቻችን የት ገቡ ብለው ሊጠይቁ ይገባል ሲሉ ምሁራን ገለጹ፡፡
Next articleየአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ ዛሬ መቐለ ገቡ፡፡