Home Uncategorized ወደ ትግራይ እየገባ ያለው እርዳታ አነስተኛ መሆኑን የትግራይ እርሻና  የተፈጥሮ ሃብት ልማት...

ወደ ትግራይ እየገባ ያለው እርዳታ አነስተኛ መሆኑን የትግራይ እርሻና  የተፈጥሮ ሃብት ልማት አስታወቀ፡፡

515
0

——-

በያዝነው ወር ወደ ትግራይ እየገባ ያለው እርዳታ ካለፈው ወር ሲነፃፀር አነስተኛ መሆኑን የትግራይ እርሻና  የተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ኣትንኩት መዝገቦ ገለፁ፤ የቢሮ ኃላፊው በእርዳታ ጉዳይ ዙርያ ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ሰብዓዊ ዕርዳታ ወደ ትግራይ ህዝብ እንዲገባ የቶክስ ኣቁም ውሳኔ መደረጉ ተከትሎ ባለፉት ወራት ወደ ትግራይ የገባው የእርዳታ እህል በቂ ባይባልም እንደጅምር የሚበረታታ ነበር ብለዋል የትግራይ እርሻና የተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አትንኩት መዝገቦ፡፡

ዶ/ር ኣትንኩት ኣክለውም የተላከው እርዳታም ወደ ህብረተ-ሰቡ እንዳይዳረስ ፋሽስቱ እያደረገው ባለው የማደናቀፍ ስራ በነዳጅ እጦት ምክንያት ወደ ህዝቡ ማዳረስ እንዳልተቻለና ህዝቡም ለከፍተኛ ኣደጋ ተጋለጦ እንደሚገኝ ይገልፃሉ፡፡

2021 የአውሮፓዊያን አቆጣጠር የእርዳታ ሂደቱ በስድስት ዙሮቸ መሸፈን እንደነበረበት ያወሱት የቢሮ ኃላፊው በሌሎች የአገሪቱ ክልሎች ስድስቱ ዙሮች ተጠቃለው የ2022 ለመውሰድ በዝግጅት ላይ መሆናቸው አስረድተዋል፡፡

ወደ ትግራይ እየተላከ ያለው ግን በ2021 በስድስት ዙሮች መግባት ከነበረበት የሶስተኛው ዙር መሆኑን የገለጡት ዶክተር አትንኩት ይህ ባለፈው ታህሳስ ወር መጠናቀቅ የነበረበት እስካሁን በአግባቢ ሊላክ አለመቻሉን አመልክተዋል፡፡

የኣውሮፓ ህብረተ በቅርቡ ወደ  ትግራይ በመምጣት ያለውን አሰከፊ ሁኔታ ከተመለከተ በኋላ ከፋሽስቱ ቡድን ጋር መነጋገሩንና በየወሩ ሁለት ሚሊዮነ ሊትር ነዳጅ እንደሚፈቅድ መገለፁ ያወሱት ዶክተር አትንኩት በተግባር የታየ ለውጥ እንደሌለና ወደ ትግራይ ነዳጅ አለመግባቱን በመግለፅ ህዝቡን መታደግ አልተቻለም ብለዋል፡፡

ሰብዓዊ ዕርዳታን ለፖለቲካዊ ፍጆታ መጠቀም ወንጀል ነው የሚሉት ዶ/ር አትንኩት ስለሆነም በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ የዓለም ማህበረ-ሰብ በመመልከት አፋጣኝ እርምጃ መወሰድ ይኖርበታል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም በተለያዩ የውጭ አገራት የሚገኙ ዲያሰፖራው ማህበረ-ሰብ በትግራይ ህዝብ እየደረሰ ያለው ጀኖሳይድ የአለም ማህበረ-ሰብ እንዲያውቀው እያደረጉት ያለው ጥረት በማድነቅ እርዳታን የማደናቀፍ ተግባሩ አጠናክሮ የቀጠለበት መሆኑን የአለም ማህበረ-ሰብ እንዲያውቀው ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

በመዓዛ መኮነን 

Previous articleየትግራይን ህዝብ ከተጣለበት ክልከላ ለመውጣት ሌላኛውን አማራጭ እንዲጠቀም የሚያስገድዱ ሁኔታዎች ሊታሰብባቸው ይገባል ተባለ፡፡
Next articleበተመድ የተቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን ከፋሽስቱ የአብይ ቡድን ጋር ለመስራት መወሰኑ ለገለልተኛነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው ተባለ።