Home ዜና ዘንድሮ የሚከበረዉን የንቦች ቀን በትግራይ ቀኑን ታስቦ እንዲዉል የሚያስችል ሁኔታ አለመኖሩን ተገለፀ፡፡...

ዘንድሮ የሚከበረዉን የንቦች ቀን በትግራይ ቀኑን ታስቦ እንዲዉል የሚያስችል ሁኔታ አለመኖሩን ተገለፀ፡፡  

886
0

ዘንድሮ የሚከበረዉን የንቦች ቀን የፋሽስቱ አብይ ቡድን ሰራዊትና ግብረ አበሮቹ በትግራይ በከፈቱት የጀኖሳይድ ጦርነት ሳብያ በትግራይ ቀኑን ታስቦ እንዲዉል የሚያስችል ሁኔታ አለመኖሩን የዘርፉ ተመራማሪዎች ገለጹ፡፡

የጠላት ሃይሎች በዘርፉ ያደረሱት ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን እና ይህም የትግራይን ህዝብ በድህነት ተዘፍቆ እንዲኖር ከማለማቸዉ የተነሳ መሆኑን ጭምር አስረድተዋል፡፡

ወራሪና ተስፋፊ ሃይሎች ከአፍሪቃ  ቀንድ አምባገነን መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ሰራዊት ጋር በማበር በትግራይ ህዝብ ላይ ባወጁት የጀኖሳይድ ጦርነት በተለያዩ መሰረተ ልማቶች ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸዉን አይዘነጋም፡፡ በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ የማር ማጣርያ ማሽን የነበረዉና ወደ ተለያዩ የአለም ሃገራት ምርቱን በማቅረብ የሚታወቀዉ ዲማ የማር ምርት ማጣርያና የንብ እርባታ ፋብሪካ ጠላቶች  ሙሉ በሙሉ አዉድመዉትና ዘርፈዉት መሄዳቸዉን ይታወቃል፡፡

በትግራይ የንብ ምርት ላይ የደረሰዉን ዘርፈ ብዙ ጉዳት በማህበረ-ኢኮኖሚያዊ፤  ስነ-ልቦናዊ ጉዳት ሲታይ  በህዝቡ፣ በሰራተኛዉና በተመራማሪዉ ላይ ትልቅ ጠባሳ ጥሎ ማለፉን በትግራይ እርሻ ምርምር ማእከል የንብ እርባታ ተመራማሪዎች ገልፀዋል፡፡

በተለያዩ የአለም መገናኛ ብዙሃን “ወርቃማ ፈሳሽ ማር” እየተባለ የሚጠራዉ የትግራይ ማር ለማጥፋትና ለማዉደም በጠላት ሃይሎች ሆን ተብሎ ታቅዶና ታልሞ የተሰራ ሰይጣናዊ ድርጊት ነዉ፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆንም በምርቱ ላይ ከፍተኛ የስም ማጠልሸት ስራ እየተሰራ ነዉ፡፡ በምርቱ ብቻ ሳይሆን በአየር ንብረት ለዉጥም ከፍተኛ ጠቀሜታ የነበረዉ የትግራይ የማር  ምርት ለምርቱ ግብአትነት የሚያገለግሉ ተፈጥሯዊና ዘመናዊ መሳርያዎች መዉደማቸዉንም አክለዉ ገልፀዋል፡፡

በ2013ዓ.ም በትግራይ የተካሄደዉ የጀኖሳይድ  ጦርነት የጠላት ሃይሎች ለጦርነቱ አመቺነት ይጠቀሙበት የነበረዉን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የትግራይን የማር ምርትና የንቦች እርባታን ክፉኛ ጎድቶታል፡፡ ይህ ያደረጉበት ዋነኛ አላማም የትግራይን ንፁህ ማርና ምርት በአለም ገበያ ተወዳጅና ተመራጭ መሆኑን ስለሚያዉቁ በዚህም ትግራይና ህዝቧ የድህነት አረንቋ ዉስጥ ተዘፍቆ ሰብአዊ እርዳታን የሰማይ ደጅ እንዲሆንበት ለማድረግ የታለመ እኩይ ተግባር መሆኑን ተመራማሪዎቹ አስረድተዋል፡፡

ሁል ግዜ በየአመቱ ግንቦት ወር ላይ በአገር ደረጃ ሆነ በአለም የንቦች ቀን እየተባለ ይከበር የነበረ ቢሆንም እንኳን የዘንድሮዉ ግን በትግራይ መከበር ቀርቶ ቀኑን ታስቦ የሚዉልበት ሁኔታ እንኳን የለም፡፡ ሆኖም ግን ትግራይ ያፈራቻቸዉ በዘርፉ ያሉ ተመራማሪዎች ሃብታም ስለሆነች ወደፊት ስለሚሰሩ ስራዎች በማሰብና በማቀድ ቀኑን ማሳለፍ እንደሚቻልም ተመራማሪዎቹ አስገንዝበዋል፡፡

በተጨማሪም በዘረፉ የደረሰዉ ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዉ የትግራይ ህዝብን አእምሮና እውቀት እስካልወሰዱት ድረስ ከነበረበት በላቀ ደረጃ በህብረትና በአንድነት መስራት እንደሚቻል በትግራይ እርሻና ምርምር ማእከል የዘርፉ ተመራማሪዎች ጠቁመዋል፡፡

በሙሉብርሃን ዳርጌ   

Previous articleየኦሮሞ ነፃነት ግንባር በተለያዩ ፖሊስ መምሪያዎች ታስረው የሚገኙ የአመራር ኣባላቱ በአፋጣኝ ከእስር እንዲፈቱ ጠየቀ፡፡
Next articleለጋሽ ድርጅቶች እጃቸውን ካልዘረጉ በአፍሪካ ቀንድ በሚልዮኖችን   በረሃብ ሳቢያ በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኙ የተ.መ.ድ አስጠነቀቀ።