Home ዜና የመብት ተማጔቾች ሪፖርት

የመብት ተማጔቾች ሪፖርት

670
0

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን በትግራይ ተወላጆች ላይ የተፈፀመው ወንጀል ከጦር ወንጀልና በሰብአዊነት ላይ ከሚፈፀም ወንጀሎች ጋር የሚስተካከል መጠነ ሰፊ ወንጀሎች መፈፀማቸው Humanrightswotch and Amnesty international አስታወቁ፡፡ ሁለቱም አለማ አቀፍ የመብት ተማጓቾች ዛሬ ባወጡት መግለጫ የአማራ ባለስልጣናት፣ የአማራ ልዩ ሐይል፣ የአማራ ሚሊሻና የፌዴራል ፀጥታ ሀይሎች በወንጀሉ ተጠያቂዎች መሆናቸው አረጋግለዋል፡፡

ጉዳዩ እጅግ በጣም አሳሰቢ መሆኑን የገለፁት ሁለቱም ተቋማት ሰላም አስከባሪ ሃይል ወደ ምዕራብ ትግራይ እንዲሰማራም ጠይቀዋል’ Humanrightswotch በምእራብ ትግራይ በተፈፀመው ዘር የማፅዳት ወንጀል የአማራ ባለስልጣናት፤ የአማራ ልዩ ሀይል፣ የአማራ ሚሊሻና የፈደራል ፀጥታ ሀይሎች ተጠያቂዎች አድርጓል፡፡Humanrightswotch የአማራ የፀጥታ ሀይሎች በምእራብ ትግራይ ዞን ፀረ ሰብአዊነትና ዘር የማፅዳት ወንጀል መፈፀማቸውን አረጋገጠዋል፡፡

Humanrightswotch ይዞት በወጣው 89 ገፅ ያለውን የምርመራ ሪፖርት ላይ እናንተን ከዚህ መሬት እናጠፋቹሀለን የሚል ርእስ የያዘ ነው፡፡Humanrightswotch ሪፖርት ጎይተኦም የተባለ በምእራብ ትግራይ የምትገኝ ዓዲ ጎሹ በተባለ መንደር ሰሊጥ፣ ማሽላና ጥጥ በማምረት ይተዳደር የነበረውን የ42 ዓመቱ የጉዳቱ ሰለባ የሆነው አርሶ አደር በመጥቀስ እንዳመለከተው በአማራ ልዩሀይልና ሚሊሻ ከመኖሪያ ቤቱ ተወስዶ ለወራት ያህል መታሰሩን ጠቅሰዋል፡፡

በአማራ የአከባቢው ባለስልጠናትና የፀጥታ ሀይሎች በአርሶ አደሩ ላይ ዛቻና ማስፈራራት ሲበዛበት ከጥቃቱ ለማምለጥ ወደ ጫካ መግባቱን Humanrightswotch በሪፖርቱ አመላክተዋል፡፡በጫካ ቆይቶ ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲመለስ በዓዲ ጎሹ ይኖሩ የነበሩ በርካታ የትግራይ ተወላጆች ሰብስበው ተከዘ ወንዝ አሻግረው እንዳባረርዋቸው ሪፖርቱ አመልክተዋል፡፡ከቀናት በኋላ በዓዲ ጎሹ የኖሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆች ቁጥር ከመመናመኑ በተጨማሪ በአከባቢው እንደማይፈቀድላቸውና መኖሪያ አከባቢያቸው በሌላ ሰፋሪዎች መወሰዱን ሪፖርቱ አመላክተዋል፡፡አሁን ሁኔታው ሲያስታውሰው ፍርሀት እንደሚሰማው የገለፀው ጎይተኦም በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች በአማራ ተስፋፊ ሀይሎች የደረሰባቸውን ስቃይና በሀይል የመፈናቀል እጣ ፈንታ የደረሰበት መሆኑንም የ Humanrightswotch ሪፖርት ያመለክታል፡፡ጎይተኦም የዓለም ማህበረ-ሰብ ከእይታ ከራቀባቸው የምእራብ ትግራይ ተፈናቃያዎች እጣ ፈንታ ከደረሰባቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ተጎጂ የትግራይ ተወላጆች መካከል አንዱ ነው ብለዋል፡፡

የፌደራል መንግስት ወታደሮች ምእራብ ትግራይን በመውረር ከትግራይ ሀይሎች ጋር ግጭት በተቀሰቀሰበት ወቅት በሞቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ከመኖሪያ ቤታቸው እንዲፈናቀሉ ዛቻና ማስፈራራት የጥሰት ዘመቻዎችና ከመኖርያ ቀያቸው የማባረር ችግር እንዳጋጠማቸው ሪፖርቱ አመላክተዋል፡፡በምእራብት ትግራይ ነዋሪዎች ላጋጠመው በሀይል የማፈናቀል፣ ፆታዊ አመፅና ጥቃት አስገድዶ መድፈር ከህግ ውጭ መግደልና ሌሎች ፆታዊ ጥቃቶች የአማራ የፀጥታ ሀይሎችና በአማራ ስር የተቋቋመው የወልቃይት ኮሚቴ የተባሉ ተጠያቂዎች መሆናቸውን በሪፖርቱ አመላክተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ሰፊ የሰብል ምርት፣ የቤት እንስሳ መዘረፋቸውና የትግራይ ተወላጆች መኖሪያ ቤት በሌሎች መያዙና የገቢ ምንጭ የነበሩ ተቋማትም እንዲውድሙ መደረጉን ሪፖርቱ አመልክተዋል፡፡Humanrightswotch በሪፖርቱ እንዳመለከተው በትግራይ ተወላጆች ላይ የጅምላ እስራት በስውርና በሚታወቅ እስር ቤት እንዲታሰሩ እንዲገደሉ፣ እንዲገረፉ የተደረጉ ከመሆኑ በተጨማሪ ከመሰረታዊ አገልግሎቶችና ሰብአዊ እርደታ እንዳይደርሳቸው መደረጉን አመልክተዋል፡፡

የትግራይ ተወላጆች መንነታቸውን ያነጣጠረ ጥቃት እንደደረሰባቸው ያመለከተው ሪፖርቱ በተለይም በአካል ጉዳተኞችና የእድሜ ባለ ፀጎች የጉዳቱ ዋና ሰለባዎች መሆናቸውን በሪፖርቱ ተጠቅሰዋል፡፡የአማራ ፀጥታ ሀይሎች ከፌደራል ፀጥታ ሀይሎች ጋር በመሆን በትግራይ ተወላጆች ላይ በፈፀሙት የተቀናጀ ጥቃት በርካታ የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸው አስረድተዋል፡፡ Humanrightswotch and Amnesty international በጋራ ባወጡት ሪፖርት በምእራብ ትግራይ በተፈፀመው ዘር የማፅዳት ወንጀል የአማራ ባለስልጣናት፣ የአማረ ልዩ ሀይል፣ የአማራ ሚሊሻና የፈደራል ፀጥታ ሀይሎች ተጠያቂዎች አድርጓል፡፡

መብራህቱ ይባልህ

Previous articleየትግራይ ውጭ ጉዳዮች ቢሮ መግለጫ
Next articleየትግራይ ውጭ ጉዳዮች ፅ/ቤት መግለጫ