Home ዜና የመጀመሪያው የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፊሰር ምትኩ ሃይለን የ2021 የዓለም የእርሻ ሽልማት ሎሬት...

የመጀመሪያው የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፊሰር ምትኩ ሃይለን የ2021 የዓለም የእርሻ ሽልማት ሎሬት ብሎ መምረጡን አስታወቀ።

992
0

የእርሻና ተፍጥሮ ሳይንስ ከፍተኛ ትምህርት ግሎባል ኮንፌደረሽን የመጀመሪያው የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፊሰር ምትኩ ሃይለን የ2021 የዓለም የእርሻ ሽልማት ሎሬት ብሎ መምረጡን አስታወቀ።   

የሽልማት ስነ-ስርዓቱ ሰሞኑን በቻይናው ናንጀንግ የእርሻ ዩኒቨርስቲ የሚከናወን ሲሆን በኢንተርኔት ለዓለም ማህበረ-ሰብ በቀጥታ ይሰራጫል ተብሏል።

ፕሮፌሰር ምትኩ ሃይለ ለዚሁ የሎሬትነት ሽልማት የበቁት በእርሻ የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርትና ሳይንሳዊ ምርምር ባበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ መሆኑን ኮንፌዴረሽኑ ባሰራጨው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

ፕሮፌሰር ምትኩ ሃይለ የመጀመሪያው የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሆነው ያገለገሉ ምሁርና ተመራማሪ ናቸው።

የመቐለ ዩኒቨርስቲ መስራችና የመጀመሪያው የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ምትኩ ሃይለ እ.ኤ.አ ከ1992 – 1993 የያኔው አለማያ ያሁኑ ሃሮማያ ዩኒቨርስቲ የአካዳሚ ም/ፕሬዝዳንት በመሆን ያገለገሉ ሲሆን እ.ኤ.አ በ1993 በአዲስ የተቋቀመውን የመቐለ አሪድ ኮሌጅ ዲን ሆነው ተሾሙ። ኮሌጁን ወደ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ቀጥሎም ወደ ዩኒቨርስቲ በማሳደግ (ከ2000-2011) ዪኒቨርስቲውን የመሩ ሲሆን  እ.ኤ.አ  ከ2011 -2015 በኢትዮጵያ የዩኔስኮ ምክትል ቋሚ ልኡክ በመሆን ያገለገሉት ፕሮፌሰር የመጀመሪያና ዲግሪያቸውን በእፅዋት ሳይንስ ሁለተኛ ዲግሪያቸው ከአ.አ ዩንቨርስቲና ከአለማያ ዩኒቨርሲቲ .በ1980፣ በ1983 በተከታታይ እንዲሁም በ1988 በአፈር ሳይንስና /ሶይል ሳይንስና ላንድ ኢቫሉዬሽን ከጌንት ዩኒቨርስቲ ፒ ኤች ዲያቸውን ተቀብለዋል።

ፕሮፌሰር ምትኩ ሃይለ

ፕሮፌሰር ምትኩ ከ30 ዓመት በላይ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአመራርነት ቦታ ያገለገሉ ሲሆን የትምህርት ተቋማት በመገንባት፣ በሰው ሃይል ልማት እና በትግራይ ዘላቂ ልማት ለማረጋጥ ባበረከቱት አስተዋፅኦና ባሳደሩት ተፅእኖ እውቅና አግኝተዋል፡፡

 ካበረከቱት አስተዋፅኦ መካከል ዋነኛው የመቐለ ዩኒቨርስቲን በመመሥራትና በአመራሮች በአገሪቱ ልማት እንደመጣ ያበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ተጠቃሽ ነው።

ፕሮፌሰር ምትኩን በተመለከተ የአገር ውስጥና የውጭ ምሁራን በሰጡት ምስክርነት መቐለ ዩኒቨርስቲን በመመሥረትና በማስፋፋት አሁን ከደረሰበት 30 000 ተማሪዎችን የመቀበል አቅም እንዲኖረው በማድረግ ከኢትዮጵያ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲ መካከል አንዱ እንዲሆን ያደረጉ ናቸው።

ፕሮፌሰር ምትኩ ከአመራርነት ባሸገር በማስተማርና የፒ ኢች ዲ እና ድሕረ  ፒኢችዲ ተማሪዎችን በማማከር ብዙ ምሁራን ኢትዮጵያውያን ያበቁ ሲሆን የፕሮፌሰር ራእይና አመራር የመቐለ ዩኒቨርስቲን በነበረው ውስን ሃብት ተጠቅመው ከአመሠራረቱ ጀምሮ ወደ ላቀ ዩኒቨርስቲ በማሳደግ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋል ።

ኮንፌዴረሽኑ በተመሳሳይ ቤልጅየም የሚገኘው የጌንት ዩኒቨርስቲ ባልደረባ የኤሜራተሱ ፕሮፌሰር ማርክ ቫን ሞንታጎን የ2021 የዓለም የእርሻ ሽልማት ተሸላሚ እንደሆኑ መርጧቸዋል።

Previous articleፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል(ዶክተር) በላኩት ደብዳቤ በትግራይ የሰብአዊ እርዳታ ካለው ችግር አንጻር የሚመጣጠን አይደለም ብለዋል፡፡  
Next articleየትግራይ መንግስትበመርህ ላይ የተመሠረተ የሰላም ድርድር ላይ ለመሳተፍ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ለመላክ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ።