Home ዜና የማህበራዊ የትስስር ገጾች ውሎ

የማህበራዊ የትስስር ገጾች ውሎ

541
0

የፋሽስቱ ቡድንና የአማራ ተስፋፊ ሀይሎች  ባለፉት አስራ ስምንት ወራት በምእራብ ትግራይ የፈጸማቸው ወንጀሎች እንዳይታወቅባቸው መረጃን የማጥፋት ስራ እየሰሩ  ስለ መሆናቸው እና በትግራይ ህዝብ ላይ እየቀጠለ ያለው ጀኖሳይድ ይቁም የሚሉ ሀሳቦች የዛሬ የማህበራዊ ሚድያ ትኩረት ካገኙ ጉዳዮች መካከል ናቸው፡፡

ዛሬ በማህበራዊ ሚድያ ከፍተኛ ትኩረት ካገኙት ጉዳዮች መካከል የአማራ ተስፋፊ ሀይል በምእራብ ትግራይ በርካታ የጅምላ መቃብር አገኘሁ ብሎ ያሰራጨው ዘገባ ነው፡፡

ዘገባውን አስመልክቶ አስተያየታቸውን የሰጡት የማህበረ-ሰብ አንቂዎች የፋሽስቱ ቡድን እና የአማራ ተስፋፊ ሀይሎች ባለፉት አስራ ስምንት ወራት በምእራብ ትግራይ የፈጸማቸው ወንጀሎች እንዳይታወቅባቸው መረጃን የማጥፋት ስራ እየሰሩ ቢሆንም ይህ ግን ቀድሞ የከሸፈ ሴራ ነው ብሎታል፡፡

ምክንያታቸው ሲያስቀምጡም በትግራይ ለተፈጸመው ጀኖሳይድ አጣሪ ቡድን እንዳይቋቋም እና የተባበሩት መንግስታት ላቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን በጀት እንዳይመደብለት ሲወተወት የከረመው ፋሽስቱ እነዚህ ሲከሽፉበት አሁን በእጁ የቀረቹን ብቸኛ መንገድ መረጃን የማሸሽ ተግባር እየሰራ ነው በማለት ጽፏል፡፡

የጠፋብህን ንብረት ከሌባው ጋር ሆነህ ከፈለከው መቼም አታገኘውም እንደሚባለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትግራይ ጀኖሳይድ በገለልተኛ አካል ይጣራል ማለቱን ተከትሎ ወንጀለኛው መረጃን የማጥፋት ስራ እየሰራ መሆኑን በርካቶች በስፋት እየተጋሩት ነው፡፡

አስገራሚ ነገር ሁሌም የሰውን ለቅሶ ለመቀማት የማይቀደመው የአማራ ተስፋፊ ሀይል የጅምላ መቃብር ማንነት የአማራ ተወላጆች ነው ቢልም እውነታው ግን የፋሽስቱ ቡድኑ በምእራብ ትግራይ የሰራቸው ወንጆሎች እንዳይታወቅበት 51 ሺህ የትግራይ ተወላጆች አጽም ሰብስቦ የማሸሽ ስራ እየሰራ መሆኑን በተለያዩ የትስስር ገጾች እየተሰራጨ ነው፡፡

ትግሃት ሚድያ በበኩሉ ከምእራብ ትግራይ ተፈናቅሎ ደብዛቸው የጠፋው ከአንድ ሚሊዮን በላይ የትግራይ ተወላጆች መልስ የተገኘ ይመስላል በማለት ጽፏል፡፡

የአፍሪካ ጉዳዮች የፖለቲካ ተንታኝ ማርቲን ፕላውት በካናዳ ኦቶዋን የምትኖር የትግራይ ተወላጅ ዳያስፖራ ቤተሰቦቼ በህይወት ይኑሩ እይኑሩ የማውቀው ነገር የለም በማለት ትግራይ ውስጥ ያለውን ችግር የገለጸችውን ጽሁፍ በትዊተር ገጹ አጋርቷል፡፡

በዩክሬን ጦርነቱ በጠፎ ሁኔታ ቢቀጥልም አስፈላጊ የሰብአዊ እርዳታ እያዳረስን ነው በማለት የጻፈው ደግሞ የተባሩት መንግስታት ድርጅት የህጻናት አድን ድርጅት uncef ነው፡፡ በትግራይ ግን ፋሽስቱ ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ እየተጠቀመ ስለሆነ ጦርነት ሳይኖርም እርዳታ ለማድረስ ፍቃደኛ አለመሆኑን  የትግራይን ህዝብ ለማጥፋት ካለው እቅድ ነው በማለት በትስስር ገጾች ሲንሸራሸር ውሏል፡፡

France24 በበኩሉ በትግራይ በተጣለው ከበባና ክልከላ ምክንያት በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለተጠቁ እርጉዝ እናቶችና ህጻናት ይሰጥ የነበረው የምግብ አቅርቦት በማለቁ በርካቶች ለሞት እየተዳረጉ ነው፡፡ ስለሆነም አስቸካይ መፍትሔ ያስፈልጋል በማት የተጸፏው ጽሁፍ በርካቶች ሲቀባበሉት ተስተውለዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በትግራይ ጾታዊ ጥቃት ለደረሶባቸው ሴቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ አስራ አምስት የሴቶች ተቋማት ስለ መጠየቃቸውም ሌላኛው የማህበራዊ ሚድያ ትኩረት ነው፡፡ 

በመጨረሻም በኢትዮጵያና በኬንያ ድንበር አካባቢ በመንግስት ሀይሎችና በታጣቂዎች መካከል ግጭት እንደነበር BBC አስነብቧል፡፡ ኢትዮጵያ በፋሽስቱ ቡድን እየተመራች ትግራዋይን ለማጥፋት የተጀመረው እቅድ አሁን ላይ መላ አገሪቱን ትርምስ ውስጥ እንደከተታት የዛሬ የማህበራዊ ሚድያ ትኩረት የሳቡ ጉዳዮች ናቸው፡፡

ይብራህ እምባየ

Previous articleሀገር እንድትቀጥል ከተፈለገ ሁሉን ያካተተ ሀገራዊ ውይይትና ምክክር ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ተነገረ፡፡
Next articleበምዕራብ ትግራይ የዘር ማፅዳት፣ የጦር ወንጀሎች እና በሰብአዊነት ላይ ወንጀል መፈፀሙ ተረጋገጠ