Home ዜና “የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች”

“የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች”

704
0

ፋሽስት አብይ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በሚከሰቱ ግጭቶችና ሰው ከነህይወቱ በእሳት ተቃጥሎ በሚሞትባት ሃገር እንዲሁም የትግራይ ህዝብ በረሃብ እንዲያልቅ በፈረደበት ወቅት በሶማሊላንድ ሃርጌሳ ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ሃዘኑ መግለፁ ብዙዎችን አስገርሟል፡፡


የፋሽስቱ የአብይ ቡዱን አገሪቱን ወደ ጦርነት በመማገድ የብዙ ዜጎች ህይወት በጦርነት በረገፈበት በአሁኑ ወቅት ለዜጋው ያልተጨነቀው በሶማሊላንድ ሃርጌሳ ላይ ስለተከሰተው የእሳት አደጋ ሃዘኑ መግለፁ ስለ ጤንነቱ ሁኔታ ብዙዎችን እንዲጠራጠሩ አድርጓል፡፡
የትግራይ ህዝብ በተደጋጋሚ በዱሮን እንዲደበደብ ያደረገው ፋሽስቱ አብይ፣ በቅጥረኛ ወታደሮቹና በአምባገነኑ ኢሳያስ እንዲሁም በተስፋፊ የአማራ ሃይሎች የትግራይ ሴቶች እና ልጃገረዶች ከህፃናት ጀምሮ እስከ መነኩሴ ድረስ ሲደፈሩ በወንዶች መደፈራቸው ምንም እንዳልሆነ በስላቅ መናገሩ ይታወሳል፡፡


ባለፈው ዓመት ለጀኖሳይድ ጦርነት ያዘመተው ጥምር ሰራዊት ከዳንሻ እስከ ማይካድራ፣ ከዋጃ እስከ ኮረም፣ ከዛላምበሳ እስከ ኢሮብ፣ ከሸራሮ እስከ ዓዲነብርኢድ፣ ከአክሱም እስከ ዓዲግራት፣ ከሳምረ እስከ ተምቤን ዓብይዓዲ፣ እንዲሁም ከዓዲግራት እስከ መቐለና ከማይጨው እስከ ዓዲጉደም የፋሽስቱ ወታደሮች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማውያን የትግራይ ዜጎች በግፍ በጨፈጨፉበት ወቅት ሰራዊቱ በስነ-ምግባር የተገራና በሞራል የተገነባ ይመስል ‘’አንድም ሰው አልገደለም ’’ በማለት ለህዝብ ያለውን ንቀት በግልፅ ያሳየበት አጋጣሚ ነበር፡፡


ፋሽስቱ የአብይ ቡዱን በትግራይ ህዝብ ላይ በከፈተው የጀኖሳይድ ጦርነት ተከትሎ ምንም አይነት የሰብአዊ እርዳታ እንዳይገባ በከለከለበት ወቅት የትግራይ ህዝብ እንደ ዜጋው ሳይቆጥርና ሃዘን ሳይሰማው ስለሶማሊላንድ ተጨንቆ ሃዘኑ መግለፁ ‘’ የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች ‘’ እንደሚባለው ብዙዎችን አስገርሟል፡፡


የገዛ ሃገሩ ዜጋ በዘሩ እየተለየ ከነህይወቱ በእሳት እንዲቃጠል እየተደረገ እያየ ትንፍሽ የማይል፣ ሰላማውያን ዜጎች በውድቅት ሌሊት በዱሮን የሚደበድብ፣ በዋነኛነት ደግሞ የትግራይ ህዝብ በረሃብ አለንጋ እየተገረፈ እንዲሞት የፈረደ የጭካኔ ጥግ የተላበሰ ስብእናው እንዴት በሃርጌሳ ስለተከሰተው ቃጠሎ ስሜቱ ሊነካ ይችላል በማለት የጤንነቱ ሁኔታ አጠራጣሪነት የሚገልፁም በርካቶች ናቸው፡፡


ሃገሪቷ ሰላም ርቆባት ዜጎችዋ በሰላም ወጥተው ወደ ቤታቸው ስለሚመለሱበት ሁኔታ በሚናፍቁበት ወቅት ወጣቶች ወደ ትምህርት ቤት ከመሄድ ይልቅ ወደ ጦርነት በሚማገዱባት አገር፣ ፋሽስቱ አብይ የሰላም ሰባኪ ይመስል ስለዩክሬንና ሩሲያ ጦርነት አስስጨንቆት እነዚህ አገራት ችግሮቻቸው በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ሲጠይቅ መሰማቱም አስገራሚ ያደርገዋል፡፡

ተካ ጉግሳ

Previous articleበትግራይ የሚገኙ የትምህርት ተቋማት መውደማቸውን ተከትሎ በተማሪዎች ስነ ልቦና ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩ ተነገረ፡፡
Next articleየትግራይ   መካነ ኢየሱስ ቤተ-ክርስቲያን  ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ-ክርስቲያን  ግንኝነቱ ማቋረጡን አስታወቀ፡፡