Home ዜና የተጎጋ ጥቃት ሰለባዎች  የሰማእታት ቀን አንደኛ አመት ተከበረ ፡፡

የተጎጋ ጥቃት ሰለባዎች  የሰማእታት ቀን አንደኛ አመት ተከበረ ፡፡

604
0

የተጎጋ ጥቃት ሰለባዎች  የሰማእታት ቀን አንደኛ አመት ተከበረ ፡፡

——

ፋሽስታውያንና ወራሪ ሀይሎች የትግራይን ህዝብ ለማንበርከክ  ሰላማውያን ሰዎችን  በግፍ መጨፍጨፍ ዋና ትኩረት አድርጎ እየሰሩበት መሆኑን በሰማእታት ቀን ጉዳት የደረሰባቸው የህብረተ-ሰብ ክፍሎች ገለጹ፡፡

የትግራይ ሰራዊት አባላት በበኩላቸው ጠላቶቻችን በሰማእታት ቀን የሚፈጽማቸው ድብደባዎችና ግድያዎች የሰማእታትን አላማ  ከማሳካት እንደማያግዳቸው አስታወቁ፡፡

ባለፈው አመት ሰኔ ወር ላይ ልክ በዛሬዋ የሰማእታት ቀን ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ደቡብ ምስራቅ ዞን ቶጎጋ ከተማ በገበያ ቀን በፈጸመው የአየር ድብደባ የጉዳቱ ሰለባ ከሆኑት መካከል ህጻን ኤልዳ አንዷ ናት፡፡

ህጻን ኤልዳና በወቅቱ ሆድዋ ላይ ጉዳት ደርሶባት ወደ ሆስፒታል መምጣት ብትችልምፋሽስቱ በጣለው ክልከላ ምክንያት በመድሃኔት እጦት ሳቢያ ህይወቷ አልፏል፡፡ ፋሽስታውያንና ወራሪ ሀይሎች የትግራይን ህዝብ ለማንበርከክ ሰላማውያን ዜጎችን በግፍ መጨፍጨፍ የተለመደ ተግባራቸው በመሆኑ በቶጎጋ ከተማ በገበያ ቀን በህዝቡ ላይ  የቦንብ ናዳ ማዝነባቸውን የህጻን ኤልዳና ወላጆች ይናገራሉ፡፡

ባለፈው አመት በቶጎጋ ከተፈጸመው ጥቃት በተጨማሪ ሰው በላው የደርግ ስርአት የትግራይን ህዝብ ስነ ልቦና ለመስበርና ህዝቡን ለማንበርከክ  በሚል ከንቱ ምኞት በ1980 ዓ/ም በሓውዜን ከተማ በገበያ ቀን የአየር ድብደባ በመፈጸም ከሁለት ሺህ አምሰት መቶ በላይ ሰላማውያን ሰዎች ህይወት መቅጠፉ የሚታወስ ነው፡፡

 ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላም ትግራይን ለማንበርከክ በማደርገው ጥረት እንቅፋት ይሆንብኛል ያላቸውን በ2011 ዓ/ም ጀነራል ሰዓረ መኮንን እና ሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ እንዲገደሉ አድርጓል፡፡  

ይህን ግፍ የፈጸሙ ግፈኞች በፍትህ አደባባይ ቀርበው ተገቢውን ቅጣት እንደሚያገኙ  ለትግራይ ህዝብ ህልውናና ደህንነት ሲሉ ክቡር መስዋእትነት የከፈሉ ጀግኖች ሁሌም ሲታወሱ ይኖራሉ  የሚሉት የጀግናው የትግራይ ሰራዊት አባላት ጠላቶቻችን የትግራይን ህዝብ  ለማንበርከክ በሰማእታት ቀን የሚፈጽማቸው ድብደባዎችና ግድያዎች ሰማእታቶቻችን የተሰውለት አላማ  ከማሳካት ፍጹም አያግደንም ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ባለፈው አመት የውስጥና የውጭ ሀይሎች የጋራ ግንባር ፈጥረው እንደ ህዝብ ሊያጠፉን የዘመቱብንን ፊት ለፊት ገጥመን በጀግናው አፍሪካዊው ጀነራል ራስ አሉላ አባነጋ ስም በተሰየመው ዘመቻ ጠላቶቻችን ከትግራይ አብዛኛውን አካባቢ ተጠራርገው እንዲወጡ በማድረግ  ድሉ  በደማቅ በአል  አክብረነዋል ያሉት የትግራይ ሰራዊት አባላት፡፡ 

ዘንድሮ 34ኛው የሰማእታት ቀን ስናከብር ደግሞ በወራሪዎች ቁጥጥር ስር የሚገኙ  የትግራይን ግዛታዊ አንድነት በሰላማዊ መንገድ አልያም በሌላ መልኩ ነጻ  እናደርጋለን ብለዋል፡፡

ይብራህ እምባየ

Previous articleሩሲያና ቻይና ፋሽስቱ በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጠረውን የረሃብ ቸነፈር አፋጣኝ መፍትሄ እንዳያገኝ ማደናቀፋቸው ማርክ ሎውኮክ ገለፁ፡፡
Next articleፋሽስት የአብይ ቡድንን ጨምሮ ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ የሚጠቀሙ መንግስታት  ተጠያቂ የሚያደርግ ውሳኔ  ፀደቀ፡፡