Home ዜና የትግራይን ቀውስ እንዲያበቃ ሁሉም በጋራ ድምጻችን ማሰማት አለብን – ሳማንታ ፓወር

የትግራይን ቀውስ እንዲያበቃ ሁሉም በጋራ ድምጻችን ማሰማት አለብን – ሳማንታ ፓወር

768
0

ሳማንታ ፓወር ከእርዳታ ለጋሽ ሃገር ሚንስትሮች ጋር በትግራይ ጉዳይ ውይይት ማድረጋቸውን በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ትግራይ ላይ የፈጠረውን ቀውስ እንዲያበቃ ትኩረት ሰጥተን በጋራ ድምጽ የምናሰማበት ጊዜ አሁን ነው ያሉት ሳማንታ ፓወር፤ የትግራይን ቀውስ በአስቸኳይ እንዲፈታና አስፈላጊውን እርዳታ በሚፈለገው መጠን እንዲገባም ርብርብ ማደረግ እንደሚስፈልግ የተናገሩት ሳማንታ ፓወር የተቋረጡ መሰረታዊ የህዝብ አገልግሎቶች ወደ ነበሩበት እንዲመለሱና አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በቅርቡ የሶማልያ ፕሬዚዳንት ሆኖ ለተመረጡት ሀሰን ሸክ ማህሙድ የእንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላለፉ፡፡

ዶክተር ቴድሮስ ይህን መልእክት ያስተላለፉት የሀሰን ሸክ ማህመድ የበዓለ ሲመትን መከበር ምክንያት በማድረግ ነው፡፡

በቀጣይ ጤና ለሁሉም የሶማሊያ ህዝብ በማዳረስ ረገድ አብረን እንደምንሰራ ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

አዲሱ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሸክ ማህመድ ሶማልያን ለመምራት  ለሁለተኛ ጊዜ  የሶማልያ ህዝብ እሳቸውን በመምረጡ ህዝቡ በእሳቸው ላይ እምነት በማሳደሩ ምስጋና አቀርበዋል።

ሀሰን ሸክ ማህሙድ ከሁለት ሳምንታት በፊት  የቀድሞ የሶማልያ ፕሬዚደንት እና ከፋሽስቱ ቡድን ጋር በማበር በትግራይ ጀኖሳይድ የተሳተፈው መሀመድ ፎርማጆን በከፍተኛ ድምፅ አሸንፈው መመረጣቸው ይታወቃል፡፡

Previous articleየፋሽስቱ ቡድን  በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች ያሰማራቸው ቅጥረኛ ሰራዊት በንፁሃን ዜጎች ላይ እየፈፀሙት ያለውን ግድያ፣ እንግልት፣ ቤት ንብረት ማቃጠልና ማውደም ከምንግዜም በላይ ተጠናክሮ መቀጠሉን ነዋሪዎች ገለፁ፡፡ 
Next articleፋሽስቱ የአብይ ቡድን አገሪቷን ወደ ጦርነት በማስገባቱ የአገሪቱ ብር የመግዛት አቅምም በ26% ወርዷል ተባለ፡፡